null It is said that the corporation should plan to enter into a competitive market for the sugar consumption of the community.

የመንግስት የልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴው የስኳር ኮርፖሬሽን የ2010 በጀት ዓመት የ11 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም እና የ2011 በጀት ዓመት ዕቅድ ሪፖርት ገምግሟል፡፡

ኮርፖሬሽኑ ከዚህ በፊት 3 ወደ 8 ፋብሪካዎች ከፍ ብሎ ሲያመርት የቆየ፣ በተጀመሩ በርካታ የማስፋፊ ፕሮጀክቶች በበጀት ዓመቱ የአገዳ፣ የስኳርና ሞላሰስ ምርቶችን ለማምረት የተሞከረ ቢሆንም ኮርፖሬሽኑ በምርት ማምረት ሂደትና በፕሮጀክት ስራ ላይ በተፈጥሮ አደጋ፣ ከፍተኛ ዝናብ፣ የግብዓት እጥረትና በጸጥታ ችግር እንደተፈለገው ማምረት እንዳልተቻለ የኮርፖሬሽኑ ዋና አስፈጻሚ አቶ እንዳወቅ አብቴ ገለጹ፡፡

የአሰራር ስርዓቶች ዘርግቶ የሰራተኞችን ክፍተት ለመሙላት እንዲሁም በመስኖ አጠቃቀም፤በመሬት ዝግጅት፤ በአገዳ አቅርቦት፤የማሽነሪ የጥገና አቅም እና የግብዓት አጠቃቀም መሻሻል አሳይŸልም ብለዋል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው ኮርፖሬሽኑ በካይዘን ትግበራ ላይ እየተሰራ ያለው ስራ እንደ ጠንካራ ጎን የተነሳ ሲሆን በሸንኮራ አገዳ ልማትና በፋብሪካዎች በስኳር ማምረት የጀመሩ ፋብሪካዎች በሙሉ አቅም እያመረቱ እንዳልሆነ ምክኒያት ነው ያሏቻን የማምረቻ ግብዓት እጥረት፣ የጸጥታ ችግርና የፋብሪካዎች ዘግይቶ መጀመሩን ኃላፊዎች ተናግረዋል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው እንዲሁም በፋብሪካዎች ማስፋፊያ ግንባታ ለረጅም ጊዜ ሲጓተት የቆየ መሆኑ ለአብነትም በኩራዝ ቁጥር አንድ እና በጣና በለስ እስካሁን አጠናቆ ለምርት ዝግጁ ማድረግ ካለመቻሉም ባሻገር ውሳኔ ተሰጥቶ ለሌሎች ኮንትራክተር እንዲሰጥ ለሚመለከተው ቢተላለፍም እስካሁን ያልተቋጨ መሆኑ የአመራሮች ቁጥጥር የላላ መሆኑን ያሳያል ቢባልም ፕሮጀክቶች መጀመሪያ ተጠንተው ያለመጀመር ችግሩ እየገዘፈ እንዲመጣ አድርጓል ያሉት ደግሞ ዋና አስፈጻሚ አቶ እንዳወቅ ናቸው፡፡

በበጀት ዓመቱም የህብረተሰቡን የስኳር ፍላጎት ለማሟለት ከውጭ አገርና በአገር ውስጥ የተመረቱ ባጠቃላይ አምስት መቶ ሰላሳ ዘጠኝ ሺ ሰባት መቶ አስራ አምስት ቶን ስርጭት የተደረገ ቢሆንም የኮታ ማነስ፣ የክልሎች ቅንጅታዊ አሰራር የላላ መሆንና የሸማች ህብረት ስራ ማህበራት በትኩረት ማነስ በህብረተሰቡ ዘንድ ክፍተት እንዲኖር ማድረጉን ቋሚ ኮሚቴው ገምግሟል፡፡        

በመጨረሻም ኮርፖሬሽኑ የሚታይበትን አቅም ውስንነት ቀርፎ አመራሩ ችግር ፈቺ በሆነ መንገድ በማቀድ ቅድሚያ መስጠት ለሚገቡ ስራዎችን በመለየት ካለበት ውስንነት ወጥቶ የአገር ውስጥ ፍላጎት አሟልቶ ኤክስፖርት ወደ ማድረግ ደረጃ ለመድረስ መሰራት እንዳለበትም አንስተው በታቀደው እቅድ ላይም የተነሱ ጉዳዮችን መከለስ እንዳለባቸው ቋሚ ኮሚቴው አሳስቧል፡፡