null Medication centre for #COVID-19 victims close to accomplishment

በሚሊኒየም አዳራሽ በመንግስት በመዘጋጀት ላይ ያለው የኮቪድ 19 የህክምና መስጫ ማዕከል በመጠናቀቅ ላይ መሆኑ ተነገረ፡፡

ሚያዚያ 17 ቀን 2012 ዓ.ም (ዜና ፓርላማ) ይህ የተገለጸው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈፃጸም መርማሪ ቦርድ በሚሊኒየም አዳራሽ በመዘጋጀት ላይ ያለውን የኮቪድ 19 የህክምና መስጫ ማዕከልን በጎበኘበት ወቅት ነው፡፡ 

በጉብኝቱ ወቅት የማዕከሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር ኢስማኤል ሸምሰዲን ለቦርዱ አባለት የማዕከሉን ዝግጅት አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ማዕከሉ 1‚000 ህመምተኞችን የሚይዝ የመኝታ፣ ከታካሚዎች ንኪኪ ነጻና የራሱ መግቢና መውጫ ያለው የምግብ ማብሰያ፣ የላብራቶሪና የላውንደሪ ክፍሎች ያሉት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ 28 አልጋዎች ለፅኑ ህሙማን (ICU) መዘጋጀታቸውንና 17 ቬንትሌተር በዛሬው እለት እንደሚገጠምላቸውም ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም አዳራሹ 6 በሮች ያሉት በመሆኑ የህመምተኞች መግቢና መውጫ ተለይቶ መዘጋጀቱን፣ ታካሚዎች በእግር እንዲንቀሳቀሱ ሰፊ ኮሊደር እንዲኖረው መደረጉን፣ የከፋ ችግር ቢከሰት ሌሎች 1‚000 አልጋዎችን የሚይዝ ሰፊ ቦታ መኖሩንም ገልጸዋል፡፡

ታካሚዎች ከቤተሰቦቻቸው ጋር መገናኘት ስለማይችሉ በስካይፒ በታብሌቶች እንዲገናኙ ለማድረግ እንዲሁም እንዲዝናኑና መረጃዎችን እንዲያገኙ ቴሌቪዥኖችን የመግጠም ስራዎች እንደሚሰሩም አክለዋል፡፡

በቀጣይ አጭር ጊዜያት ውስጥም የአየር ማስገቢና ማስወጫ፣ የእጅ መታጠቢና ተንቀሳቃሽን ጨምሮ ወደ 70 የሚጠጉ መፀዳጃዎች ዝግጅት እንደሚጠናቀቅም ገልጸዋል፡፡ የህክምና ማዕከሉ አለማቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ለመድረግም ከፍተኛ ጥረት እንደሚደረግም ነው ያብራሩት፡፡

ስራው ከፍተኛ ጥንቃቄና ሀላፊነትን የሚጠይቅ በመሆኑ ለማዕከሉ የተመለመሉ ሰራተኞች በስራ አፈጻፀማቸው የተሻሉ ናቸው የተባሉትን መሆኑን ነው ለቦርዱ አባላት ያስረዱት፡፡

በሌላ በኩል በግቢው የውሀ ቢኖርም ወደ አዳራሹ ውስጥ የተዘረጋ የውሀ መስመር  አለመኖሩን በችግርነት ጠቁመው፣ ለሀኪሞች ማረፊ የሚሆኑ ሆቴሎች በቅርቡ የሚገኙበትና ለመረጃ ልውውጥ ተግባር የሚውሉ 30 ዎኪ ቶኪ ስልኮች የሚመቻቹበት ሁኔታ እንዲፈጠርም ጠይቀዋል፡፡

የቦርዱ አባላት በጉብኝቱ ማብቂያ ላይ በሰጡት አስተያየት በአጭር ጊዜያት ውስጥ እነዚህ በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን አድንቀዋል፡፡

የቦርዱ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ጴጥሮስ ወ/ሰንበት በበኩላቸው በማዕከሉ በኩል በእጥረት የተነሱ ነጥቦችን ቦርዱ ነቅሶ በማውጣትና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር የሚፈቱበትን መንገድ እንደሚፈልግ ጠቁመው፡ እስካሁን