null MoFA: The State diplomacy is being elevated to preserve the national interest ever greater.

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የ2010 የዘጠኝ ወራት የስራ አፈፃፀም ሪፖርቱን ለምክር ቤቱ አቅርቧል፡፡

በውይይቱ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን የ9 ወራት የዕቅድ አፈፃፀም ያቀረቡት ሚንስትሩ ዶክተር ወርቅነህ ገበየው እንደተናገሩት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለግማሽ ዓመት ያቀዳቸውን ተግባራት ለማከናወን የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል፡፡

በአፍሪካና ቀንድ አካባቢ ዘላቂ ሰላም፣ ልማትና ኢኮኖሚ ትስስር መፍጠር፣ የአፍሪካ ህብረት ለአህጉሪቱ ልማት፣ ሰላምና ውህደት መሳሪያ ሊሆን በሚችል ሁኔታ እንዲጠናከር ማስቻል፣ በሁለትዮሽ ግኑኝነታችን አጋሮችን ማጠናከር፣ በባለ ብዙ ወገን መድረኮች የአገሪቱን ተደማጭነት በማጠናከር የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ፣ የጸጥታና ሌሎች ጥቅሞችን ከማስጠበቅም በተጨማሪ የዲፕሎማሲ አድማሶችን ለማስፋትም እየተሰራ መሆኑን ሚንስትሩ ገልጸዋል፡፡

ም/ቤቱ በበኩሉ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን የሚደርስባቸውን ችግር እና የመብት ጥሰት ችግሮች እንዲፈቱ ከሚሲዮኖች ጋር በትብብር በመስራት ከ41ሺ በላይ የሚሆኑ ዜጎችን መብታቸው እንዲከበር፣ ከእስር እንዲፈቱ፣ ከስደት እንዲመለሱና የሰሩበትን ገንዘባቸው እንዲያገኙ መደረጉን በጠንካራ አፈጻፀም አንስቷል፡፡

ምንም እንኳን ዲያስፖራው በሀገሩ ልማት ተሳትፎ እያደረገ ቢገኝም ከብዛቱ አንጻር ዲያስፖራው የሚኖርበት አካባቢ የማወቅ፣ የመመዝገብ እና ልዩ ልዩ አደረጃጀት ውስጥ በማሳተፍ አገሪቱ ከዘርፉ ማግኘት የሚገባትን ጥቅም እያገኘች በለመሆኑ ቀጣይ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ መሆኑ ውይይቱ ተነስቷል፡፡

በውጭ ግኑኝነት ወሳኝ ሚና የሚኖራቸውን ጉዳዮችን በመለየት በጥናት ላይ የተመሰረተ ዲፕሎማሲ በማካሄድ በተለይም በአባይ ውሃ አጠቃቀም ላይ አገሪቱ ልትከተለው በሚገባት አቅጣጫና ከቀጠናው ሰላም ጋር በተገናኘ ሊወሰዱ በሚገቡ ሂደቶች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እንዲሰራ ምክር ቤቱ አሳስቧል፡፡ 

ምክር ቤቱ በውሎ ሶስተኛ ዓመት የስራ ዘመን ሃያ አምስተኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ ጉባዔ እና የተፈጥሮ ሃብት ልማትና አካባቢ ጥበቃ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢነርጂ አዋጅን ለማፅደቅ ከቋሚ ኮሚቴ የቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡