null New installation technologies are underway for wider public participation on legislative process.

በምክር ቤቱ ስራዎች ላይ ህብረተሰቡ ቀጥታ ተሳትፎ እንዲኖረው ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ውጤቶች በስራ ላይ ዋሉ፡፡

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህገ-መንግስታዊ ተልዕኮ ተግባራትና መረጃዎች በዳበረ የዲሞክራሲ ስርአት እንዲገነቡ ምክር ቤቱን ተደራሽ ከማድረግ ረገድ በስፋትና በጥራት ሊሰራ እንደሚገባ ተጠቆመ፡፡

የምክር ቤቱ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ይፋ ማድረጊያ መድረክ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ሙፈርሃት ካሚል የተከፈተ ሲሆን የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚንስቴር ሚንስትር ወ/ሮ ኡባህ መሃመድ እንዲሁም ተጋባዥ እንግዶችና ባለ ድርሻ አካላት በተገኙበት የሪባን ቆረጣ ስነ ስርአት ተካሂዷል፡፡ በእለቱም የለሙ ቴክኖሎጂዎች ተመርቀው ለአገልግሎት ዝግጁ መሆናቸው ይፋ ሆንዋል፡፡

በሃገራችን የዳበረ የዲሞክራሲ ስርአት እንዲረጋገጥ እና የጎለበተ የፓርላማ ዲሞክራሲ ስረአት እንዲገነባ ምክር ቤቱን ይበልጥ ተደራሽ የሚያደርጉ ስራዎችና ህገ መንግስታዊ ተልኮዎች ላይ ህብረተሰቡን ተሳታፊ ለማድረግ የምክር ቤቱን አሰራር ለማዘመን እና ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ዜጎች ሃሳባቸውን እንዲገልጹ ብሎም የምክር ቤቱ አባላት ከመረጣቸው ህዝብ ጋር በቀጥታ በቴሌ ፕረዘንስ ውይይት በማድረግ፣ በምክር ቤቱ በሚወጡ ረቂቅ አዋጆች ላይ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ቪዲዮ ኮንፍረንስ ባለበት ቦታ ሆኖ ውይይት ማድርግ እንዲችሉ፣ የማእከል አገልግሎት፣ የጥቆማ አስተዳደር ስርአት፣ ስማርት ፎን፣ ሞባይልና የሌጅስሌቲቭ አፕልኬሽን አገልግሎት እንዲሁም ህብረተሰቡ ነጻ የስልክ ጥሪዎችን በመጠቀም  ሃሳቡን እና ያሉትን ጥያቄዎች በስፋት እንዲገልጽ የሚያስችሉ ስራዎች ተመርቀው አገልግሎት እንዲሰጡ ተደርጓል፡፡

ተያይዞም እነዚህ አገልግሎቶች የተጠናከረ የህዝብ ተሳትፎ እንዲኖርና ቴክኖሎጂውን በመጠቀም ህብረተሰቡ በምክር ቤቱ ስራዎች ላይ በንቃት በመሳተፍ በሃገራችን የጎለበተ የፓርላማ ስርአት እንዲገነባ እና ለዜጎች ሰብአዊ መብት መከበርና ለዲሞክራሲ ስርአት ግንባታ ያለውን ሚና ሊጫወት ይገባልም ተብሏል፡፡