null Plan and Development Commission were not undertaking the country's mission.

ፕላንና ልማት ኮሚሽን የተጣለበትን አገራዊ ተልዕኮ በአግባቡ እየተወጣ እንዳልሆነ ተገለጸ፡፡

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 45ኛ መደበኛ ስብሰባ የፕላንና ልማት ኮሚሽንን የ2011 በጀት ዓመት የ10 ወራት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ገምግሟል፡፡ ምክር ቤቱ ኮሚሽኑ ባቀረበውን ሪፖርት ላይ ክፍትት እንዳለበት በዝርዝር የጠቆመ ሲሆን የ10 ወራት እቅድ አፈጻጸሙንም ዝቅተኛ ነው ብሏል፡፡

የሁተኛውን እድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ የመካከለኛ ዘመን አፈጻጸም ግምገማ የተገኘው እድገት የተሻለ ቢሆንም የገቢ ንግድ እቃዎችን በአገር ውስጥ ለመተካት፣ የውጭ ምንዛሬ እጥረቱን ለማስተካከል እና በስራ እድል ፈጠራ የተደረገው ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ውስንነት የነበረበት መሆኑን ምክር ቤቱ ከቀረበው ሪፖርት መገንዘብ ችሏል፡፡

በተመሳሳይም የሁለተኛውን እድገትና ትራንስፎርሜሽን ግቦችን ለማሳካት ሲደረግ በቆየው ጥረት በግብርና፣ በኢንዱስትሪ፣ በቱሪዝም እና በማዕድን ዘርፎች ላይ በርካታ የአሰራር ክፍተቶት እንደነበሩ ነው በሪፖርቱ የተገለጸው፡፡

በ2010 በጀት ዓመት የአገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት 7.7 በመቶ የተመዘገበ ሲሆን የ2011 በጅት ዓመት የኢኮኖሚ እድገቱን ለመገመት የሚያስችል ሙሉ መረጃ ባይጠናቀርም የተቀመጠውን የ11.0 በመቶ የኢኮኖሚ እድገት ማሳካት እንዳማይቻል የሚያመለክቱ የአፈጻጸም ጉደለቶች እንዳሉ ምክር ቤቱ ተገንዝቧል፡፡

የፕላንና ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር ወ/ሮ ፍጹም አሰፋ ባቀረቡት ሪፖርት እንደገለጹት በሁተኛው እድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ የመካከለኛ ዘመን አፈጻጸም ግምገማ የመንግስት ሜጋ ፕሮጀክቶች አፈጻጸም ግልጽ አለመሆን፣ ህገወጥ ንግድ እና የሙስና አሰራር መበራከት እንዲሁም የዋጋ ግሽበቱ ከ2011 ታህሳስ ወር ጀምሮ የመጨመር አዝማሚ ማሳየቱ ህብረተሰቡን ተስፋ ያስቆረጡ ጉዳዮች መሆናቸውን በተደጋጋሚ በተካሄዱ መድረኮች የተነሱ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በቀሩት ሁለት አመታት የሁለተኛው እድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ይዘት ላይ ለመወሰን የሚያስችል ሰነድ ተዘጋጅቶ ከአስፈጻሚ መስሪያ ቤቶች ጋር ሰፊ ውይይት የተደረገበት መሆኑንና የዋጋ ግሽበቱን ለመቆጣጠር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን እተሰራ መሆኑን ነው ኮሚሽነሯ በሪፖርታቸው ያመለከቱት፡፡

አያይዘውም የዘርፍ አስፈጻሚ መስሪያ ቤቶች የሁለተኛውን እድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ አፈጻጸም እና አመታዊ እቅድ በወቅቱ አለማቅረብ፣ የእቅድ ጥራት ጉድለት እና ባቀዱት ልክ ባለመፈጸማቸው የኮሚሽኑ የ2011 በጀት አመት የ10 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ዝቅተኛ ሊሆን እንደቻለ አመልክተዋል፡፡

በኮሚሽኑ ከፍተኛ የሰው ሀይል ፍልሰት፣ የግዥ መጓተት እና ከደመወዝ ማነስ አንጻር ብቃት ያለው ሰው ለመሳብ ተግዳሮቶች እንዳሉም ኮሚሽነሯ አክለዋል፡፡

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የገቢዎችና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ ለምለም ሀድጎ በሰጡት ግብረ መልስ ኮሚሽኑ ለአገሪቱ የሚጠቅሙ የተለያዩ ጥናቶች ማድረጉን፣ በሁለተኛው እድገትና ትራንስፎርሜሽን ዙሪያ ከስፈጻሚ መስሪያ ቤቶች ጋር ውይት ማካሄዱን እና የተቋሙን ስራ ለህዝብ ተዳራሽ ለማድረግ የኮሚኒኬሽን ስትራቴጂ መነደፉን በጥንካሬ አንስተዋል፡፡

በሌላ በኩል የተቋሙ የ10 ዓመት መሪ እና የ2011 በጀት አመት እቅድ ላይ ውስንነቶች እንዳሉ፣ ወቅቱን የጠበቀና ከእቅድ ጋር ያልተናበበ ሪፖርት በሚያቀርቡ አስፈጻሚ መስሪያ ቤቶች ላይ ተጊቢነት ያለው አርምጃ አለመወሰዱን እንዲሁም የኮሚሽኑ የበጀት አፈጻጸም 59 በመቶ መሆኑን የተከበሩ ወ/ሮ ለምለም በክፍተት አመላክተዋል፡፡