null Questions and complaints at the time of the irreversibility of the teaching of the university are under risk.

የሚነሱ ጥያቄዎችና ቅሬታዎች በወቅቱ ያለመመለስ በዩኒቨርስቲ በመማር ማስተማር ሂደት ላይ እንቅፋት እየሆነ ስላለ በትኩረት መሰራት አለበት ተባለ፡፡

የኢፈደሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴው የዲላ ዩኒቨርስቲውን የ9 ወራት የስራ አፈጻጸማቸውን በዝርዝር ለማየት የመስክ ምልከታ አድርጓል፡፡

ዲላ ዩኒቨርስቲ በአሁን ሰዓት የመጀመሪያ ጀነሬሽን ደረጃ ተሰጥቶ የመመማረር ማስተማር ሂደተን በማጠናከር እየሰራ እንደሆና በበጀት ዓመቱ የአከባቢውን አቅም ከግምት ያገናዘበ ጥናት በማጥናት ችግር ፈቺ በሆኑ ጉዳዮችን ትኩረት በመስጠት በተለይ አከባቢው ለቡናና አግሮ ኢንዳስትሪው ሰፊ አቅም ያለበትና ምርታማ በመሆን ከአገርም አልፎ ለአለም አገራትም ጭምር ሊተርፍ የሚችል በመሆኑ ምርታማነትን ለማሳደግ መሰረታዊ በሆኑ ጉዳዮችን በምርምር ለመደገፍ በዕቅድ ተይዞ እየተሰራ እንደሆነ የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ችሮታው አየለ ገልጸዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ አክለው ቦታኒክ ጋርደን ለማልማት ከተወሰደው 133 ካሬ መሬት በ20 ካሬው ላይ በማልማት በአከባቢው እየጠፉ ያሉትን እጽዋት ዝርያዎችን ለመጠበቅና ለምርምርና ተግባር ትምህርት አጋዥ በመሆነ መልኩ ጎን ለጎንም መዝናኛ ሆኖ በቱሪዝም ዘርፍ አስተዋጽኦ ያለውን ስራ እየሰሩ መሆናቸውን ነው፡፡

ቋሚ ኮሚቴው በምልከታ ወቅት ከተማሪዎች ህብረት፣ ከሰራተኛና ከመምህራን ጋር ውይይት ያደረጉ ሲሆን ዩኒቨርስቲው ቀጣይ አገር ተረካቢ ትውልድ መፍለቂያ እንደመሆኑ ለመማር ማስተማር ሂደት ጥራቱን እንዲጠብቅ ከፍተኛ ትኩረት መሰጠት ቢገባውም በዩኒቨርስቲው በአንዳንድ መምህራን የሚሰጠው ትምህርት በተባለው ጊዜ የማይጀምርበትና የሚሰጡ የትምህርት አይነቶች በወጣላቸው መርሐ ግብር መሰረት በተከታታይ ምዘና ያለመደገፍ ሁኔታ መኖሩን ገልጸው  ለሴቶች የሚሰጥ ምንም አይነት ልዩ ድጋፍ አለመኖሩን ተከትሎ የመመረቅ ምጣኔ በዩኒቨርስቲው ዝቅተኛ እንደሆነም ገምግመዋል፡፡

ክፍተቱን እየፈጠሩ ያሉ መምህራን በሌሎች ዩኒቨርስቲዎች በተመሳሳይ ተቀጥረው በማስተማር ላይ ያሉ በመሆናቸው እንዲሁም ባደረሳቸው ጊዜ መጥተው የሚያስተምሩ እንጂ ተማሪው ማግኘት የሚገባውን ዕውቀት እንዲያገኙ የማድረግ ስራ እየተሰራ ባለመሆኑ ተማሪዎች ለውድቀትና ለመባረር ምክንያትም ጭምር መሆኑን ፕሬዝዳንቱ ለቋሚ ኮሚቴው ተጨማሪ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው በሁሉም ካምፓሶች እየተገነቡ ያሉ ግንባታዎች በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ ተጠናቀው አገልግሎት ያለመስጠት እንዳለ ሆኖ የተሰሩ ህንጻዎችም ጥራት የሌላቸውና ውሃ የሚፈሱ በመሆናቸው ለአጠቃቀም እየተቸገሩ እንደሆነ በምልከታው ወቅት ተገንዝቧል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው በዩኒቨርስቲው በተማሪዎች አገልግሎት ዘርፍ ሰፊ ቅሬታ ሲነሳ መቆየቱን ለአብነትም የመብራት መቆራረጥ፣ ንጹህ መጠጥ ውሃ አለመኖር፣ በቂ የጤና አገልግሎት አለመኖር፣ ጥራት ያልጠበቀ ምግብና ሽንት ቤት አለመኖር ሰፊ ክፍተት እንዳለ በተማሪዎች ለበርካታ ጊዜ ተጠይቆ ምላሽ አለመሰጠቱ የመልካም አሰተዳር ጥያቄ ከመሆኑም በተጨማሪ አሁን አሁን በግቢው ውስጥም የሚፈጠሩ የስርቆትና የሞባይል ስልክ ንጥቂያ ወንጀሎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ቢመጣም ተገቢው ጥበቃና ከለላ አለመደረጉ ለደህንነታቸውም ጭምር ስጋት እንደሆነ ተመልክቷል፡፡

ለደህንነት ስጋት ችግር እንደ መንስዔ ሆኖ የተነሳው የተባረሩ ተማሪዎች በግቢው ውስጥ መኖራቸው፣ በተማሪዎች መኝታ ክፍል አከባቢ ተገቢው ጥበቃ አለመኖርና አልፎ አልፎም በሌብነት ላይ የሚሳተፉ ተማሪዎችና የጸጥታ አካት መኖራቸው ችግሩን ይበልጥ አሳሳቢ እደሚያደርግ ነው፡፡

በዩኒቨርስቲው በአብዛኛው የትምህርት መስክ ቤተ-ሙከራ አለመኖር ተማሪዎች በተግባር ተደግፈው ተገቢውን ዕውቀት እንዳያገኙ ከማድረግም ባሻገር በአንዳንድ የትምህር ክፍልም ተማሪዎች ለተግባር ትምህርት መስክ እንዳይወጡ መደረጋቸውንም በወቅቱ ለቋሚ ኮሚቴው አንስተዋል፡፡ 

ቋሚ ኮሚቴው በዩኒቨርስቲው በ2008 የተደረገው ሰራተኞች የስራ ድልድል ከፍተኛ ቅሬታ ሲያስነሳ ቢቆይም እስካሁን ተገቢው ምላሽ አለመደገረጉ ሰራተኛውን ስራቸውን በሃላፊነት እንዳይሰሩና ውጤታማም እያደረጋቸው እንዳልሆነ ነው፡፡

በመጨረሻም ቋሚ ኮሚቴው ዩኒቨርስቲው ትኩረት ማድረግ በሚገባቸው በተለይ መማር ማስተማሩን በጥራት ለማስቀጠልና ተግዳሮት የሞሆኑ ጉዳዮችን በወቅቱና የሚፈታበት ስርዓት ዘርግቶ አለመስራት በውጠየታማነት ላይ እንቅፋት በመሆኑአሰራሩን በጥልቀት ሊፈትሽና ቀጣይ አቅሙን አሟጦ በመጠቀም ካለበት ችግር ለመውጣት ሌተ ቀን መስራት እንዳለበት አሳስቧል፡፡