null Speaker of the House gave press release regarding Ethiopian Human right commissioner candidate.

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ- ጉባኤ የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት እጩ ኮሚሽነር የጥቆማ ማቅረቢያ ጊዜ ና የመመዘኛ መስፈርቶችን አስመልክተው ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጡ፡፡

የካቲት 26/2011 ዓ.ም ፤ የኢትዮጵ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እጩ ዋና ኮሚሽነር ተጠቋሚዎች የሚለዩባቸውን መመዘኛ መስፈርቶችና የጥቆማ ጊዜ በማስመልከት የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ ለተለያዩ የሚዲያ አካላት በጽህፈት ቤታቸው መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

መመዘኛ መስፈርቶቹ በአዋጅ ቁጥር 210/1992 አንቀጽ 12 በተመለከተው መሰረት የሚከናዎኑ ሲሆን፤

በዚህ መሰረት፡-

  • እድሜው/ዋ/ ከ 35 ዓመት በላይ የሆነ
  • ከደንብ መተላለፍ ውጭ በሌላ የወንጀል ጥፋት ተከሶ ያልተፈረደበት
  • ዜግነቱ/ቷ/ ኢትዮጵያዊ የሆነ
  • በህግ ወይም አግባብ ባለው ሌላ ሙያ የሰለጠነ ወይም በልምድ ሰፊ እውቀት ያካበተ
  • ለሰብዓዊ መብቶች መከበር ተቆርቋሪ የሆነ
  • ለህገ-መንግስቱ ተገዥ የሆነ
  • ስራውን ለመስራት የሚያስችል የተሟላ ጤንንት ያለው
  • በታታሪነቱ ፣ በስነ-ምግባሩና በታማኝነቱ መልካም ስም ያተረፈ

የትምህርት ዝግጅትን በተመለከተ

  • ተጠቋሚው ያቀረበው ሰነድ / የልደት ዘመን፣ የትምህርት ማስረጃ፣ የስራ ልምድ እና cv /ግላዊ መረጃዎች/  ወዘተ በግብዓትነት ያቀርባል፡፡
  • በቀጥታ በህግ፣ በሰብዓዊ መብት ትምህርቶች እንዲሁም በአመራር፣ ማኔጅመንት፣ ሰላምና ደህንነት፣ የስነ-ምግባርና ስነ-ዜጋ፣ የህዝብ አስተዳደር፣ ሳይኮሎጅ፣ ሶሾሎጅና ሶሻል ወርክ፣ የሰለጠኑ ሆነው ዲግሪና ከዚያ በላይ የትምህርት ደረጃ ያላቸው እንደሚሆኑ አቶ ታገሰ በመግለጫቸው ገልጸዋል፡፡

አሰራሩ የሌሎች ሃገራት ተሞክሮን በማየት እየተሰራ እንደሚገኝ አቶ ታገሰ አብራረተዋል፡፡

ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት እጩ ኮሚሽነር የጥቆማ ማቅረቢያ ጊዜው ከመጋቢት 1 እስከ መጋቢት 20/2011 ዓ.ም ድረስ በስራ ስዓት እንደሚሆን አፈ-ጉባኤው ተናግረዋል፡፡

ማንኛውም ዜጋ የሰብዓዊ መብቴን ይከታተልልኛል ብሎ የሚያስበውን ሰው በመጠቆም መሳተፍ እንደሚችል አቶ ታገሰ ተናግረዋል፡፡

ጠቋሚዎቹ  ጥቆማቸውን ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት እጩ ኮሚሽነር አቅራቢ ኮሚቴ በሚከተሉት ዘዴዎች ማቅርብ ይችላሉ፡፡