null Special Committees of the House finished their site visit of the displaced people across the Nation.

በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች በተከሰቱ ግጭቶች የተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ አሰጣጥ በተመለከተ ከምክር ቤቱ በአካል የሚመለከቱ ቡድኖች የመስክ ምልከታ አድርገው እንዳጠናቀቁ ተገለፀ፡፡ በቀጣይም ምልከታውን በተመለከተ በምክር ቤቱ ዝርዝር ውይይት ይደረጋል ተብሏል፡፡

ይህ የተገለፀው የኢፊዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፅሕፈት ቤት ዛሬ በየካቲትና መጋቢት   ወር በምክር ቤቱ  የተከናወኑ ተግባራት እና እና የተገኙ ውጤቶች ለጋዜጠኞች ይፋ በተደረገበት ወቅት ነው፡፡

መግለጫውን የሰጡት የፅሕፈት ቤቱ ዋና ፀሐፊ ደ/ር ምስራቅ መኮንን በአገራችን አንዳንድ አከባቢዎች በተከሰቱ ግጭቶች ምክንያት የተፈናቀሉት ዜጎችን የመንግስት ድጋፍ አሰጣጥ በተመለከተ በአካል የሚመለከቱ ቡድኖች ከምክር ቤቱ አካላት በማዋቀር ወደስራ እንደተላኩ እና ያከናወኑት ምልከታ ተጠናቆ ለህዝብ ይፋ ይሆናል ተብሏል፡፡

ደ/ር ምስራቅ በዛሬው መግለጫቸው ምክር ቤቱ ባለፉት ሁለት ወራት ያከናወናቸው ተግባራት እና የተገኙ ውጤቶች ለጋዜጠኞች አብራርተዋል፡፡ በዚህ መሰረትም ምክር ቤቱ በየካቲት እና መጋቢት ወራት 6 መደበኛ እና 1 ልዩ ስብሰባ ያደረገ ሲሆን በነዚህ ስብሰባዎቹም 16 ረቂቅ አዋጆች አፅድቋል፡፡ ሌሎች 12 ረቂቅ አዋጆችም ለዝርዝር ምርመራ ለቋሚ ኮሚቴዎች መርቷል ብለዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ምክር ቤቱ የአራት ሚኒስቴር መስሪያቤቶችን እና የብሔራዊ ባንክን የ8 ወራት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት አድምጧል፡፡ ምክር ቤቱ ከፌደራል ዋና ኦዲተር ጋር በመሆን የኦዲት ግኝት ያለባቸው የፌደራል መንግስት መስሪያቤቶች በሁለት ወራት ግዜ መፈታ የሚገባቸውን ግኝቶች መፍትሔ እንዲሰጡ የሚያስችል አቅጣጫ አስቀምጧል ተብሏል፡፡

የምክር ቤቱ አባላትም በየካቲት ወር ወደየምርጫ ክልላቸው በመሄድ ከመረጣቸው ህዝብ ጋር ተገናኝቷል ያሉት ደ/ር ምስራቅ ቋሚ ኮሚቴዎች በበኩላቸው የመስክ ምልከታዎችን፣ በረቂቅ ሕጎች ላይ የህዝብ ይፋዊ የውይይት መድረኮችን፣ የኦዲት ግኝት መድረኮችን አካሂደዋል ብለዋል፡፡

የፓርላማ ዲፕሎማሲን በተመለከተ ምክር ቤቱ ከአመሪካ፣ ቱርክ፣ አርሜንያ፣ ካናዳ እና አውስትራሊያ የተወከሉ የመንግስት ሐላፊዎች ጋር በጋራ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት እንደታከሄደ ተገልጧል፡፡ በአፍሪካ-ካሪቢያን እና ፓስፊክ አገራትና አውሮፓ ሕብረት መደበኛ ጉባዔ ተሳትፎ እና በፓን አፍሪካ መደበኛ ጉባዔም ተሳትፎ እነደተደረገ ተብራርቷል፡፡

ዋና ፀሐፊዋ ዶ/ር ምስራቅ ምክር ቤቱ በአከናወናቸው ስራዎች የተገኙ ውጤቶት ሲያብራሩ የሀገሪቷ የተላያዩ የልማት ፕሮጀክቶች ወጪ መሸፈኛ የሚሆን ብድር በዝቅተኛ ወለድና በረዥም የመክፈያ ግዜ ላመግኘት ተችሏል ብለዋል፡፡

ኢንቨስትመንት፣ ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን እነዲሁም በባህል ዘርፍ ከተላያዩ የአፍሪካ፣ ኤስያ እና ላቲን አሜሪካ አገሮች ጋር በትብብር ለመስራት የሚስችል አሰራሮች እንዲዘረጉ የሚያስችሉ ሁኔታዎች እንደተፈጠሩም ተገልጧል፡፡

የምርጫ ቦርድ አደረጃጀትና አሰራር በማሻሻል እና የህገ መንግስት እና ፌዴራሊዝም አስተምህሮን ለማጎልበት የሚያስችሉ እና የመንግስትን ጉዞ የሚደግፍ ምቹ ህጋዊ እና ተቋማዊ ሁኔታዎችም ተፈጥሯል ተብሏል፡፡