null Standing committee of the House said that Jigjiga University should work with Industries to strengthen practical education.

የጅግጅጋ ዩኒቨርስቲ ለተግባር ተኮር ትምህርት መጠናከር  ከኢንዱስትሪዎች ጋር ያለውን  ግንኙነት ማስፋት እንዳለበት  የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ ገለፀ ::

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቴክኖሎጂና የሰው ሀብት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በዩኒቨርስቲው ግንባታዎች፣ ቤተ ሙከራና በዩኒቨርስቲው  የሚገኘውን ሪፈራል ሆስፒታል ጉብኝቷል፤ ከአመራሩና ከድጋፍ ሰጭ ሰራተኞች ጋርም ውይይት አካሂዷል፡፡

በዩኒቨርስቲው ለማህበረሰቡ አንድነት መጠናከር ከሚመለከታቸው አካት ጋር ተቀናጅቶ እየሰራ ሲሆን፤ተማሪዎች ትምህርታቸውን እንዳያቋጡ ድጋፍ መደረጉ፣ተካታታይ የትምርት ምዘና  ስርዓት ተዘርግቶ እየተሰራ መሆኑ፣የዩኒቨርስቲው ቤተ ሙከራ በዳይሬክቶሬት ደረጃ ተደራጅቶ ወደ ተግባር መገባቱን እና  በአካባቢው ለሚገኙት ትምህርት ቤቶች መፃህፍትንና የተለያዩ የትምህርት ቁሳቁሶችን ገዝቶ ድጋፍ ማድረጉን  ቋሚ ኮሚቴው በጥንካሬ አንስቷል፡፡ዩኒቨርስቲው ከ400 በላይ ተማሪዎችን ከጎረቤት አገራት ተቀብሎ ማስተማሩ ጥሩ ጅማሬ መሆንን ቋሚ ኮሚቴው ገልፆ፤ ሊበረታታና በቀጣይም ሊጠናከር ይገባልም ነው ያለው፡፡  ዩኒቨርስቲው   አገራዊ  ፋይዳ  ያላቸውን  ምርምሮችን ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ  ሲሆን ቀጣይነት ሊኖረው  እንደሚገባም የቋሚ ኮሚቴው አባል እና  የቡድኑ መሪ አቶ ሰይድ አባቡር  አስረድተዋል፡፡ 

በዩኒቨርስቲው ቤተ ሙከራዎችን በትምህርት አይነቶችና በትምህርት ክፍሎች በመለየት በቁሳቁስና በሰው ሀይል የማደራጀት ስራ ውስን መሆኑ፣ለተግባር  ተኮር ትምህርት መጠናከር  የኢንዱስትሪ ትስስር ስራዎች እንዳሉ ቢታወቅም በተለይ በዚህ ዓመት ካለው ተጨባጭ ሁኔታ  እንፃር  የኢንዱስትሪ ትስስሩ የመቀዛቀዝ ሁኔታ ታይቶበታል ነው የተባለው፤ ስለሆነም በቀጣይ ትኩረት ተሰጥቶት ሊሰራበት እንደሚገባ  አቶ ሰይድ አባቡር አክለው አመላክተዋል፡፡ 

በተጨማሪም በዩኒቨርስቲው ጠንካራ የውስጥ አሰራር ከመዘርጋት አንጻር የተሰሩ ስራዎች ቢኖሩም የፌደራል ዋና ኦዲተር ያገኛቸውን የኦዲት ግኝቶች ከማረምና የማስተካከያ እርምጃ ከመውሰድ አኳያ ውስንት እንዳለ  ነው አቶ ሰይድ የጠቆሙት፡፡  

የጅግጅጋ ዩኒቨርስቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት አቶ ኤሊያስ ኡመር በበኩላቸው  ተማሪዎች ዩኒቨርስቲዎች የእውቀት መፍለቂያና ማዕከል መሆናቸውን  ተገንዝበው ለትምህርታቸው ትኩረት ሰጥተው  እንዲከታተሉ ለማድረግ ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባ  እና  በአንዳንድ ዩኒቨርስቲዎች አልፎ አልፎ  የሚከሰቱ የፖለቲካ ግጭቶች ትክክለኛ መንስኤአቸው ምን እንደሆነ እንደ ዩኒቨርስቲ ሳይሆን እንደ አገር መታየት ያለበት ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡አክለውም  የመምህራን ፍልሰት በየጊዜው መኖሩን ጠቅሰው ለተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የውጭ አገር የትምህርት እድል ከመስጠት አኳያ ክፍተት እንዳለና  በአካዳሚክ ልማት ሂደቱ ወጥነት ሊኖር እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

የዩኒቨርስቲው የውስጥ የአካዳሚክ ምርምር ምክትል ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶ/ር አበዲ አህመድ በበኩላቸው እንደገለፁት በ2010 ዓ.ም መጨረሻ አካባቢ በነበረው አለመረጋጋት ሳብያ  አልፎ አልፎ ከግቢው ውጭ በሚመጡ ችግሮች ይከሰቱ እንደነበር እና አሁን ግን በፕሬዝዳንቱና በአመራሩ አማካኝነት ችግሮች ተፈተው የመማር ማስተመሩ ሂደት በጥሩ ሁኔታ ላይ  ይገኛል ነው ያሉት፡፡ዩኒቨርስቲው 168 መምህራንን የሚይዝ ትልቅ ደረጃውን የጠበቀ የመኖሪያ ቤት ህንፃ ቢገነባም ለሁሉም መምህራን ማዳረስ በለመቻሉ ችግሩን በመገንዘብ   መምህራን  በተመጣጣኝ ዋጋ ቤት  የሚያገኙበት መንገድ  ሊመቻች ይገባል ነው የተባለው፡፡