null State of Emergency Inquiry Board urges for careful attention of returnees.

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈፃጸም መርማሪ ቦርድ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ3ቱ ካንፓሶች ጉብኝት አደረገ፣

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 3 ካንፓሶች በለይቶ ማቆያ ከውጭ ተመላሽ ኢትዮጵያን ሰብአዊ አያያዝና የህክምና ባለሙያዎች ክብካቤ ይበልጥ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተገለፀ፡፡

ሚያዚያ 15 ቀን 2012 . በአገሪቱ የተከሰተውን የኮሮና ቫይረስን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ሲባል የተቋቋመው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈፃጸም መርማሪ ቦርድ መነሻውን ከጤና ሚንስቴር በማድረግ በአዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲ 3 ካምፓሶች በለይቶ ማቆያ (ኳራንታይን) የሚገኙትን ከውጭ ተመላሽ ኢትዮጵያውያን የሰብአዊ አያያዝ በተመለከተ የመስክ ምልከታ አድርጓል፡፡

የቦርዱ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ጴጥሮስ /ሰንበት የመስክ ምልከታው ወረርሽኙን በተመለከተ በአገር አቀፍ ደረጃ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን ለመቃኘትና ከዜጎች እየተነሱ ያሉ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲገኙ ያለመ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

የጤና ሚንስቴር ሚንስትር ዴኤታ ክብርት / ሰሀርላ አብዱላሂ በሀገሪቱ ተከሰተውን ከኮሮና ቫይረስ ለመከላከልና ለመቆጣጠር በጤና ሚንስቴር በኩል በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ቦርዱ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመስክ ምልከታ ባደረገበት ወቅት በዩኒቨርሲቲው በሚገኙ 3 ካምፓሶስች በተዘጋጀው የለይቶ ማቆያ 650 ከሳውዲ ተመላሽ ኢትዮጵያውን እንደሚገኙና ከእነዚህ ወስጥም 295 ሴቶች መሆናቸውን የለይቶ ማቆያው አስተባባሪ የሆኑት / መሀመድ እና / ቅድስት ለቦርዱ አባላት አስረድተዋል፡፡

ከሳውዲ ተመላሽ ኢትዮጵያውያን ወደ ማቆያው ከመጡ 13 ቀናቸው መሆኑንና የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት፣ የምግብ እና ከአካላዊ ንኪኪና ቅርርብ ነፃ የሆነ ለእንዳንዳቸው አንዳንድ ክፍል ያለው የመኝታ አገልጎሎት እንዲሁም በየጊዜው ተገቢው የሙቀት ልኬትና የኮሮና ቫይረስ ምርመራ እየተደረገላቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የመጨረሻው ምርመራ መደረጉንና ውጤቱም እንደታወቀ ወደቤተሰቦቻቸው የመቀላቀል ተግባራት እንደሚከናወነም ነው ባለሙዎቹ የተናገሩት፡፡

በሌላ በኩል ተገቢው ትምህርት እና አካላዊ ቅርርብና ንክኪ እንዳይኖር ለእያንዳንዳቸው አንዳንድ ክፍል መኝታ ቢሰጥም በአንድ ክፍል ውስጥ የመሰባሰብ ሁኔታ እንደሚታይም በስጋትነት አንስተዋል፡፡

የውሀ አቅርቦት፣ ከሚመከታቸው አካላት ጋር ተቀናጅቶ የመስራት፣ ለምግብ አብሳይ፣ ለፅዳትና ለጥበቃ ባለሙያዎች የመከላከያ ግብአት እጥረት እንዳለም ነው የህክምና ባለሙያዎች ያከሉት፡፡

የጤና ሚንስቴር ሚንስትር ዴኤታ ክብርት / ሰሀርላ አብዱላሂ በኩላቸው ተቀናጅቶ በመስራት ረገድ ያሉትን ችግሮች ከሚመከታቸው አካላት ጋር በመወያየት እየተፈቱ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

የቦርዱ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ጴጥሮስ /ሰንበት በሰጡት ማጠቃለያ በለይቶ ማቆያ (ኳራንታይን) የሚሰሩ ባለሙያዎች ከመደበኛ ስራ ባሻገር አገርን የሚያኮራ ከፍተኛ ሆነ የሰብአዊነት ተግባር ነው ብለዋል፡፡

በቀጣይም ከዚህ የበለጠ ፈታኝ ስራዎች ሊኖሩ ስለሚችሉ በጤና ባለሙያዎች ራሳውን መጠበቅና እርስ በርስ በመደጋገፍና በመቀናጀት መስራት እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

የጤና ባለሙያዎችም በስራ ሂደት ያጋጠሟቸውን ተግዳሮቶች ቦርዱ በአግባቡ የተረዳና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር እንዲፈቱ ጥረት እንደሚደርግም ገልፀዋል፡፡