null Tagesse Chafo, speaker of the House discussed with Cuban delegation led by Mr. Salvader salvades Messa on diplomatic bilateral issues.

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ  አቶ ታገሰ ጫፎ በኩባ ምክትል ፕሬዚደንት ሚስተር  ሳለቫዶር  ሳለቫዴስ  መሳ የተመራውን  የልዑካን  ቡድን  በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገረዋል፡፡

ግንቦት 23 ቀን 2011 ዓ.ም ፤ ኩባዊያን  ለሃገራችን ከቴክኖሎጂና ትምህርት ማጋራት  ባለፈ  ህይዎታቸውንም  ጭምር  እንደገበሩ አፈ-ጉባኤ  አቶ ታገሰ  ጫፎ  ገለጹ፡፡በ1969 ዓ.ም  በአገራችን   በተቃጣብን   ጥቃት   የኩባ   ወታደሮች   ከኢትዮጵያዊያን   ጎን ሆነው  እንደተዋደቁ አቶ ታገሰ ተናግረዋል፡፡

የሃገራችን ነጻነት ለማስከበር ሲሉ ለተዋደቁት ኩባዊያንና ለኩባ ህዝብ የተለየ አክብሮት አለን ሲሉ ለልዑካን ቡድኑ ገልጸውላቸዋል፡፡

 ለውጡን ተከትሎ በሃገሪቱ የተከናዎኑ  ፖለቲካዊ ፣ ማህበራዊ ፣ ምጣኔ ሃብታዊና ዲፕሎማሲያዊ   ጉዳዮችን አስመልክተው  ለልዑካን ቡድኑ አብራርተዋል፡፡

የፖለቲካ  ምህዳሩን ለማስፋት መንግስት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት  የፖለቲካ  እስርኞችና ጋዜጠኞች እንደተፈቱ አቶ ታገሰ ተናግረዋል፡፡

ሃገሪቱ በዲፕሎማሲው ዘርፍም ስኬታማ ስራ በመስራቷ ከጎረቤት ሃገር ኤርትራ ጋር የነበረው የረዥም ጊዜ አለመግባባት መፈታቱንም አቶ ታገሰ ጠቅሰዋል፡፡

መንግስት የሴቶችን ሁለንተናዊ ሃገራዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከመቸውም ጊዜ በበለጠ መልኩ ተግቶ እየሰራ እንደሚገኝ የገለጹት አቶ ታገሰ ፤ በከፍተኛ የመንግስት ስልጣን ውስጥ 50 በመቶ የሚሆኑት ሴት የካቢኔ አባላት እንደሆኑ ለልዑካን ቡድኑ እብርረተውላቸዋል፡፡

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ካሉት አስር ቋሚ ኮሚቴዎች መካከል ስድስቱ ቋሚ ኮሚቴዎች በሴቶች እንደሚመሩ  አቶ ታገሰ አክለዋል፡፡

ሚስተር ሳለቫዴስ ከኢትዮጵያ ጋር ያለው ሁለትዮሽ ግንኙነት ሁሉን አቀፍ በሆነ መንገድ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡

ሃገራቸው  በተፋጠነ መንገድ ወደ ልማት ሊያስገባ የሚችል የህገ-መንግስት ማሻሻያ ማድረጓን ም/ፕሬዚደንቱ  ገልጸዋል፡፡

ህገ-መንግስቱ ከመሻሻሉ በፊት የሃገራቸው ህዝብ በረቂቁ-ህጉ   ላይ በከፍተኛ ሁኔታ እንደተሳተፈበትና   86.8 ከመቶ የሚሆነት  ህገ- መንግስቱ እንዲሻል በይሁንታ እንደተቀበሉት ተናግረዋል፡፡

አቶ ታገሰ በበኩላቸው  በፓርላሜንታዊ  ግንኙነት  ፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር ፣ በትምህርትና በጤናው ዘርፍ ኢትዮጵያ  ከኩባ ልምድ በመውሰድ  እንደምትሰራ  አብራርተዋል፡፡

የኩባ መንግስትና ህዝብ በህገ-መንግስታቸው  ማሻሻያ ያደረጉት የተናበበ ሂደት  ለሃገራችን ጥሩ ተሞክሮ ይሆናል ብለዋል፡፡