null The committee of the House urged that there should Strong referral relation between Hospitals and clinics.

በሆስፒታሎች እና በጤና ጣቢዎች መካከል ጠንካራ የሪፈራል ቅብብሎሽ ሊኖር እንደሚባ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሴቶች ወጣቶች እና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አሳሰበ፡፡

ቋሚ ኮሚቴው ይህን ያሳሰበው በአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ እና በአዳማ ጤና ጣቢያ ባደረገው የመስክ ምልከታ ወቅት ነው፡፡

በሆስፒተሉ እና በጤና ጣቢያው ያለው የሪፈራል ቅብብሎሽ አለመጠናከር በተለይ የደም እጥረት ለሚያጋጥማቸው እናቶች የሚያስከትለውን ከፍተኛ አደጋ ቋሚ ኮሚቴው ከሆስፒታሉ ባገኘው መረጃ ማወቅ ችሏል፡፡

ሆስፒታሉ በአካዳሚክ እና በህክምና ዘርፍ አገልግሎት እየሰጠና በተለያዩ የህክምና ዘርፎች ሃኪሞችን እያመረተ ቢገኝም ሆስፒታሉ ሲመሰረት ለ20 ሺ ሰዎች ታስቦ የተሰራ በመሆኑ አሁን ካለበት ጫና በመነሳት አገልግሎቱን ለማሻሻል እና አከባቢውን ለማሳደግ እንዲሁም የአካዳሚክ ፍላጎቱን ለማሟላት ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንዳለበት ተመላክቷል፡፡

የሆስፒታሉ ፕሬዘዳንት ዶ/ር መኮንን ፈይሳ እንደገለጹት በአሁኑ ሰአት በተቋሙ ከሚሰጠው የህክምና እና የህክምና ትምህርት አገልግሎት በተጨማሪ ጥቃት ለደረሰባቸው ሴቶች እና ሕጻናት ከምክር እስከ ህግ አገልግሎት የሚሰጥ ማእከል መኖሩን አስረድተዋል፡፡

አያይዘውም የጨቅላ ህጻናት አገልግሎት አሰጣጥን አስመልክቶ ሲገልጹ ከዩኒሴፍ በተገኘው እርዳታ የተለያዩ ግብአቶች የተሟሉ ቢሆንም በእርዳታ ባገኟቸው ዘመናዊ ማሽኖች ዙሪያ ባለሙዎችን አሰልጥነው ወደ ስራ መግባት ላይ ግን እንደሚቀራቸው ገልጸው አሁን ባለው ሁኔታ ግን በቀን ከ40 እስከ 60 ህጻናት አገልግሎቱን እየተጠቀሙ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡

ፕሬዘደንቱ አያይዘውም በሆስፒታሉ ለኦክስጂን ብቻ በአመት 12 ሚሊየን ብር እንደሚወጣ ገልጸው ነገር ግን በ60 ሚሊየን ብር አንድ የኦክስጂን ኢንፕላንት መስራት ይቻላል በማለት እየተፈጠረ ያለውን የግብአት ብክነት አብራርተዋል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው በበኩሉ ጥቃት ለደረሰባቸው ሴቶች እና ሕጻናት ከምክር እስከ ህግ አገልግሎት የሚሰጥ ማእከል መኖሩን በጥንካሪሬ አንስቶ በሆስፒታሉ እየተሰጠ ካለው አገልግሎት አንጻር ከጤና ጣቢያዎች እና ከጤና ኤክስቴንሽኖች ጋር ያለው የሪፈራል ቅብብሎሽ ደካማ መሆን፣ የባለሙያ የመድሃኒት አቅርቦት እና የህክምና መሳሪያዎች እጥረት እንዲሁም የህንጻ ስታንዳርድ እንዲሁም ለጤና ባለሙዎች የሚሰጥ የአቅም ግንባታ ስልጠና ውስንነት ለሆስፒታሉ አሰራር ማነቆ በመሆናቸው በቅንጅት ሊፈቱ ይገባል ሲል  አሳስቧል፡፡

በሆስፒታሉ ያሉትን የህንጻ ግንባታ አገልግሎት ከማሳለጥ ረገድ እና ያለውን የአምቡላንስ እጥረት ከመቅረፍ አኳያ የከተማው አስተዳደር እና የጤና ጽ/ቤት ተገቢውን ምክክር በማድረግ እገዛ ሊያደርጉ እንደሚገባም ቋሚ ኮሚቴው አስገንዝበዋል፡፡