null The Ethiopian National Plan Commission presented its 11 months performance of the 2018 budget year to the House of People Representatives.

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ፕላን ኮሚሽን  የ2010 በጀት ዓመት በ11ወራት  ያከናዎናቸውን የስራ አፈጻጸ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቀረበ፡፡

ኮሚሽኑ በበጀት ዓመቱ 11 ወራት የአስራ አምስት ዓመታት ማለትም ከ2008 እስከ 2020 ሀገራዊ መሪ የልማት እቅድ ዝግጅት፣ የዘላቂ የልማት ግቦች ትገበራ የፋይናንስ ፍላጎት የዳሰሳ ጥናት፣ የሁለተኛው እድገትና ትራንስፎረሜሽን እቅድ 2010 በጀት የድርጊት መርሃ-ግብር ዝግጅት፣ የማይክሮ ኢኮኖሚ፣ የሀገራዊ የልማት እቅድ አፈጻጸም ክትትልና ግምገማ፣ የብሄራዊ ኢኮኖሚ አካውንት ግምት፣ የልማት ፕሮጀቶች ቅድመ ትግበራ ግምገማ፣ የልማት ፕሮጀክቶች አስተዳደር ስርዓትና የህግ ማዕቀፍ ዝግጅትና የሀገራዊ እድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ አፈጻጸም ክትትል ገምግሞ ስራውን እንዳከናወነና እያከናወነም እንደሚገኝ በሪፖርቱ ላይ ተብራርቷል፡፡

የተቋሙ ምክትል ኮሚሽን የሆኑት አቶ ጌታቸው አደም ባለፉት 11 ወራት ለመሪ እቅዱ  ዝግጅት ግብዓት የሚሆኑ በማይክሮ ኢኮኖሚ፣ በግብርና ትራንስፎርሜሽን፣ በማንፋክቸሪኒግ ኢንዱስትሪ፣ በሰው ሀብት ልማትና ትራንስፖርት መሰረተ ልማት ከኮሪያ የልማት ተቋም ጋር በመተባበር የረጅም ጊዜ ምልከታ ያላቸው ለመሪ የልማት እቅድ ዝግጅት ግብዓት የሚሆኑ የመነሻ ጥናቶች በተያዘላቸው እቅድ መሰረት እንዲጠናቀቁ አድርገናል ሲሉ ለምክር ቤት አባላት አስረድተዋል፡፡

በተጨማሪም በከተማ ልማትና ቤቶች እንዲሁም በስነ-ህዝብ ልማት ላይ ጥናቶችን ለማካሄድ የስራ መዘርዝር በማዘጋጀት ከኢትዮጵያ የልማት ምርምር ኢንስቲትዩትና የሳይንስ አካዳሚ ጋር በመተባበር ተቋሙ እየሰራ መሆኑን  ካብራሩ በኋላ በበጀት ዓመቱ ከተፈቀደው የየሩብ  ዓመቱን የፕሮግራም በጀት መሰረት በማድረግ በዝርዝር የተገለጹትን ስራዎች ለማከናወን ባለፉት 9 ወራት 31,571,823 አቅዶ 15,884,222 ወጭ በማድረግ 50.31% አፈጻጸም እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

ቋሚ ኮሚቴውም የሜጋ ፕሮጀክቶች አፈጻጸም ውጤት  በሪፖርቱ ላይ ለምን አልተገለጸም የሚሉትና የሁተኛው እድገትና ትራንስፎርሜሽን ግማሽ ዓመት አፈጻጸም ምን እንደሚመስል አልተብራራም የሚሉት ጥያቄዎች ተነስተዋል፡፤

ምክትል ኮሚሽኑም ሜጋ ፕሮጀክቶች የአመንጭነት ጥረት ችግር መኖር፣ የኮንትራክተር አቅም ማነስ፣ የፕሮጀክቶች አቅም ማስፈጸሚያ ውስንነትና የክልሎችና የፌደራል መስሪያ ቤት ባለሙዎች የክትትልና ድጋፍ ማነስ እንዳለ ጠቁመው  የሁለተኛውን እድገትና ትራንስፎርሜሽን ግማሽ ዓመት የስራ አፈጻጸም ክንውን በተመለከተም  የኮንስትራክሽኑ ዘርፍ እያደገ ቢመጣም ማኒፋክቸሪንጉ ደግሞ እየቀነሰ መምጣቱን አስረድተው መሰረተ ልማትም በሁሉም ክልሎች ፍትሃዊ ሁኖ እየተሰራ አለመሆኑን  በዝርዝር አብራርተዋል፡፡

 የበጀትና ፋይናስ ምክትል ሰብሳቢ የሆኑት ክቡር አቶ ነጋልኝ ዮሴፍ ተቋሙ የዝግጅት ምዕራፍ ስራዎች ሂደታቸውን ጠብቀው መሰራታቸው፣ ግቦችን በውጤት ተኮር ምዘና ስርዓት መሰራታቸውና ከፌደራል ባለስልጣናት መስሪያያ ቤቶች የቀረቡትን ፕሮጀክቶች ላይ የቅድመ ትግበራ ግምገማ ተደርጎ ሪፖርቱ ለመስሪያ ቤቶች መላካቸው እንደ ጠንካራ ጎን የሚታዩ ናቸው ካሉ በኋ አብዛኛው የ11 ወራት ስራዎች ሲገመገሙ አፈጻጸማቸው ተንጠልጥለው በሂደት ላይ እንደሚገኙ፣ ተቋሙ የተፈቀደለት የበጀት አፈጻጸም ዝቅተኛ መሆንና የዋና ኦዲተር አስተያየት በሪፖርቱ ላይ በሚገባ እንዳልተገለጹ ነገር ግን ለተጠየቁት ጥያቄዎች አስተያየትና ማስተካከያ እንደተሰጠ ቢገለጽም በውጭ ኦዲተር ሲፈተሸ ደግሞ ምንም ጉድለት እንደሌለው የሚጻረር ነገር ስላለ ደካማ ጎኖች ሲሆኑ  ሊስተካከሉ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል፡፡

በተመሳሳይም  የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ቻርተር አዋጅ ለማሻሻል የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ  እንደገና እንዲታይ ምክር ቤቱ  ለህግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መርቷል፡፡