null The Ethiopian Road Authority, its 2019 budget 6 months performance is low comparing the preceding years.

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የ2011 በጀት ዓመት የስራ አፈፃጸም ከሌሎች አመቶች አንፃር ሲታይ ዝቅተኛ መሆኑ ተገለፀ፡፡

ባለስልጣኑ ለአፈፃጸሙ ዝቅተኛነት የወሰን ማስከበር፣ የካሳ ክፍያ፣ የግንባታ ግብኣት እጥረትና የፀጥታ ችግሮችን በመንስዔነት አንስቷል፡፡

የኢፌድሪ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የከተማ ልማት፣ ኮንስትራክሽን እና የትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የባለስልጣን መ/ቤቱን የ2011 በጀት አመት 6 ወራት የዕቅድ አፈፃጸም ሪፖርትን ገምግሟል፡፡

ሪፖርቱን ያቀረቡት የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዋ/ዳይሬክተር ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኘ በ19 ፕሮጀክቶች 1,454 ኪ.ሜ በ32.3 ቢሊየን ብር በመገንባት ላይ መሆኑ እና በበጀት አመቱ በ6 ወራት ውስጥ በዋና መንገዶች በአመቱ 119 ኪ.ሜ ለመስራት ታቅዶ 44 ኪ.ሜ ሲሰራ ክንውኑ 15.2%፣ የዋና መንገዶችን ደረጃ ማሻሻል 36 ኪ.ሜ ታቅዶ 52 ኪ.ሜ መከናወኑን፣ 215 ኪ.ሜ የአገናኝ መንገዶችን ደረጃ ለማሻሻል በዕቅድ ተይዞ 85% መፈፀሙን፣ የአገናኝ መንገዶችን ደረጃ ለማሻሻል 215 ኪ.ሜ  ታቅዶ 86 ኪ.ሜ ብቻ መፈጸሙን ገልፀዋል።

ጥገናን በተመለከትም 362 ኪ.ሜ የመንገዶች ከባድ ጥገና በዕቅድ ተይዞ 272 ኪ.ሜ፣ 432 ኪ.ሜ የመንገዶች ወቅታዊ ጥገና ለመስራት ታቅዶ ከዚህ ወስጥ 320 መከናውኑ አፈጻጽሙ 74% መድረሱን፣ 4,399 መደበኛ ጥገና ታቀዶ 2,840 ኪ.ሜ መከናወኑን ባጠቃላይ የ6 ወራት ወራት የእቅድ አፈጻጸሙ 65% መሆኑን አብራርተዋል።

ለእቀድ አፈጻጸሙ ዝቅተኛነት የወሰን ማስከበር፣ የካሳ ክፍያ፣ የግንባታ ግብኣት እጥረትና የፀጥታ ችግሮችን በምክንያትነት አስቀምጠዋል፡፡

በሌላ በኩል ከዚህ በፊት በመንገድ ተደራሽንትና ፍትሀዊነት ዙሪያ ይነሱ የነበሩ ቅሬታዎችን ለማስወገድ የሚያስችል የጥናት ሰንድ መዘጋጅቱን፣ ኮንትራት ወስድው በጊዜ ማጠናቀቅ ባቃታችው የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር የመንገድ ስራ ተቋራችጮች ላይ እርምጃ የመወሰድ እና የመንገድ ዲዛይን ጥራትን ችግር ሊቀረፍ የሚችል ስራ መጀመሩን በሪፖርታችው አብራርተዋል።

ቋሚ ኮሚቴ ሪፖርቱን በተመለከተ በርካታ ጥያቄዎችን ያነሳ ሲሆን ለመንገድ ፕሮጀክቶች መጓተት በምክንያትንት የተነሱ የወሰን ማስከበር የመሳሰሉት ማነቆዎችን ከሚመለከታቸው ኣካላት ጋር በመነጋገርና በቅንጅት በመስራት ለምን ለመፍታት አልተቻለም? የጸጥታ ችግር በሌለባችው አካባቢዎች የሚሰሩ አዳዲስ እና የሚጠገኑ መንገዶች ለመጓተታችው ሌላ ምክንያትስ ምንድነው? የሚሉት በዋናነት ይገኙበታል።

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተርና ሌሎች የስራ ሃላፊዎች የወሰን ማስከበር ስራዎች አለመጠናቀቅ ለስራ እንቅፋት እየሆን በመምጣቱ ከክልሎች ጋር የጋራ ስምምነት መፈራረም እና የወሰን ማስከበር ስራ ሳያልቅ ወደ ጨረታ እንደማይገባ፣ የመንገድ ስራ ተቋራጮች አቅም ውስንነትም መንገዶች በተያዘላቸው ጊዜ እንዳያለቁ እንቅፋት መሆናቸውንም ምላሽ ሰጥተዋል።  

የቋሚ ኮሚቴ ንኡስ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ካሚል አህመድ ባለስልጣኑ ያዘጋጀው እቅድና የእቅድ አፈጻፀም ሪፖርት ግልጽ መሆኑን፣ የዋና መንገዶችን ደረጃ ማሻሻልና የመንገዶች ወቅታዊ ጥገና መከናወኑን፣ ከሚገነቡ 299 የመንገድ ፕሮጀክቶች ውስጥ በግማሽ መንፈቅ አመቱ 29ኙ ከእቅድ በላይ፣ 143ቱ በእቅዱ መሰረት እና 16ቱ ደግሞ በመካከለኛ ደረጃ መፈጸማቸውን፣ በ100 የመንገድ ፕሮጀክቶች ውስጥ ለ37,206 ዜጎች የስራ እድል መፈጠሩን፣ ባለስልጣኑ ወደሪፎርም ስራ መግባቱ ከዚህ በፊት የነበረውን አሉታዊ ገጽታ የሚቀይረውና በዜጎች ዘንድ ተኣማኒነትን የሚፈጥር መሆኑንና ደካማ አፈጻጸምና መልካም ስም የሌላቸው የመንገድ ስራ ተቋራጮችና አማካሪ መሀንዲሶች በጨረታ እንዳይካፈሉ የማድረግ እርምጃ መጀመሩን በጠንካራ አፈጻፀም እንስተዋል።

በሌላ በኩል 29 የውጭ ሀገር ተቋራጮች የሚገነቧቸው 66 የመንገድ ፕሮጅክቶች አፈጻፀም በአማካይ 55% ብቻ መሆኑ፣ 33 የሀገር ውስጥ ተቋራጮች የሚገነቧቸ 65 ፕሮጀክቶች ክንውን 47% እንዲሁም በውጭ ሀገር ተቋራጮች የሚገንቡ 13 እና በሀገር ውስጥ ተቋራጮች የሚገንቡ 5ቱ ፕሮጀክቶች ግንባታ አለመጀመራቸውን ጠቁምው፤ በዚህም የባልስልጣን መ/ቤቱን አፈጻጸም ከሌሎች አመቶች አንጻር ሲታይ ዝቅተኛ መሆኑን ገልጸዋል።

በመጨረሻም ባለስልጣኑ በቀጣይ ያሉበትን ድክመቶች በማረምና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት የተጓተቱ ስራዎችን ማካካስ እንዲሁም በተደጋጋሚ የህዝብ የቅሬታ ምንጭ የሆኑት የመንገድ ጥገና ስራዎች መጠናቀቅ እንዳለባቸውም አሳስበዋል።