null The Ethiopian Shipping and Logistics Service Enterprise is to serve as a backbone for supporting the country's economy and stabilizing market.

የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ድርጅት የአገሪቱን ኢኮኖሚ በመደገፍና ገበያን በማረጋጋት ረገድ የጀርባ አጥንት ሆኖ የሚያገለግል በመሆኑ በመንግስት በኩል ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ተባለ፣

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ ልማት፣ ኮንስትራክሽንና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰሞኑን በኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ድርጅት የባቦጋያ ማሪታይምና ሎጀስቲክስ ማሰልጠኛ ተቋምን ተመልክቷል፡፡

በኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት የባቦጋያ ማሪታይምና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ማሰልጠኛ ተቋም ተወካይ ዲን አቶ ግርማ ተሾመ እንዳሉት ተቋሙ ለአገሪቱ ገቢና ወጭ እቃዎች ፈጣንና ቀልጣፋ የባህር ትራንስፖርትና የሎጅስቲክስ አገልግሎት መስጠት እንዲችል የተቋቋመ የመንግስት የልማት ድርጅት መሆኑን አስረድተው የተቋቋመበትን አላማ ለማሳካት የመርከቦችን የጉዞ መስመር መጨመርና በባህር ላይ የሚሰማራውን የሰው ሃይል በተለያዩ ስልጠናዎች ማጠናከር ይጠበቅበታል ብለዋል፡፡

 

በአለም አቀፍ የማሪታይም ድርጅት ስምምነት መሰረት ማንኛውም በመርከብ ላይ የሚሰራ ባህረኛ አነስተኛ አስገዳጅ የመሰረታዊ ሴፍቲ ስልጠና እንዲወስድና አለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ሰርተፍኬት እንዲይዝ ይገደዳል ያሉት አቶ ግርማ በአገራችንም ይህንኑ ተግባራዊ ለማድረግ እንዲቻል ድርጅቱ በቢሾፍቱ ከተማ በባቦጋያ ሃይቅ ዳርቻ የማሪታይም ኢንስትቲዩትን አስገንብቶ 2002 . ጀምሮ  እስካሁን 4941  ሰልጣኞች ማሰልጠኑን ገልጸዋል፡፡

 

 

የሰልጣኞች ቅበላ ምልመላ ህግና ደንብ የተከተለ መሆኑን ያመላከቱት አቶ ግርማ ስልጠናው በአገራችን መሰጠቱ ቀደም ሲል በውጭ አገር በሚሰጠው ስልጠና ይወጣ የነበረውን ከፍተኛ ወጪ ከማስቀረቱም በላይ ከተወዳዳሪነት አኳያም ሰልጣኞች በየትኛውም አለም ተወዳድረው መስራት የሚያስችላቸውን እውቀትና ክህሎት እያገኙ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

 

አገራችን በባህር ትራንስፖርት ዘርፍ የተሻሉ ከሚባሉ አገሮች ተርታ የተመዘገበች መሆኑ በስልጠና አሰጣጡ ላይ ችግር የሌለ መሆኑን እና የሰልጣኞ ስነ-ምግባር የተስተካከለ መሆኑን ያመላክታል ያሉት አቶ ግርማ ስልጠና አጠናቀው የወጡ ሰልጣኞች ወደ ተለያዩ ሃገራት መርከቦች ላይ ለመቀጠር ሲፈልጉ በሃገራችን በዘርፉ የቅጥር አገናኝ ኤጀንሲ ባለመኖሩ መቸገራቸውንና መንግስት ለስራ እድል ፈጠራው እገዛ ሊያደርግ እንደሚገባ አመላክተዋል፡፡

 

የማሪን ሙያ ለማሰልጠን በዘርፉ የመምህራን እጥረትበማሰልጠኛ አካዳሚው ለስልጠና አጋዥ የሆኑ የተለያዩ መፅሃፍት አለመኖራቸው፣ ውሃ ላይ በተግባር ልምምድ በሚደረገው ስልጠና የባቦጋያ ሃይቅ እየቀነሰ በመምጣቱ ለስልጠናው እንቅፋት መሆኑና በቀጣይም የሃይቁ የመኖር ህልውና አደጋ ላይመሆኑ መንግስት ለዘርፉ ልዩ ትኩረት  ሊሰጠው ይገባል ሲሉም የተቋሙ አመራሮች፣ አሰልጣኞችና ሰልጣኞች አሳስበዋል፡፡

 

 

ቋሚ ኮሚቴው በበኩሉ ተቋሙ በዘርፉ የቅጥር አገናኝ ኤጀንሲ እንዲቋቋም፤ የአካዳሚው ማሳፋፊያ ቦታ ርክክብ እንዲፈጸም፤ የባቦጋያ ሃይቅ እየቀነሰ የመምጣቱ ምክንያት በጥናት ተለይቶ ከስጋት አደጋ የሚወጣበት ሁኔታ እንዲመቻች ጠንክሮ መስራት እንዳለበት አሳስቦ ዘርፉ የአገሪቱን ኢኮኖሚ በመደገፍና ገበያን በማረጋጋት ረገድ የጀርባ አጥንት ሆኖ የሚያገለግል በመሆኑ በመንግስት ለማሰልጠኛ ተቋሙ ትልቅ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል በማለት አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡