null The FDRE President, H.E Mrs. Sahileworq Zawede said that “ tells that the peoples of Ethiopia are well known of his ability to distinguish the wheat from the chaff”.

“የኢትዮጵያ ህዝብ በታሪኩ የሚታወቀው በአርቆ አስተዋይነቱና ስንዴውን ከገለባው በመለየት ብቃቱ ነው” ሲሉ የኢፌዴሪ ፕሬዘዳንት ወ/ሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ ተናገሩ፣

መስከረም 26 ቀን 2012 ዓ.ም. 5ኛው የህዝብ ተወካዮችና የፌደሬሽን ምክር ቤቶች አምስተኛ አመት የስራ ዘመን በጋራ ባካሄዱት መክፈቻ ስነ-ስርዓት ተከፍቷል፡፡

ፕሬዘዳንቷ በመክፈቻ ስነ-ስርዓቱ ላይ ተገኝተው የመንግስታቸውን አቋም አስመልክተው ባሰሙት ንግግር አገራዊ ለውጡ መልካም የሆኑ ፖሊቲዊና ኢኮኖሚያዊ ድሎች የበለጠ የሚሰፉበት፣ ባለፉት ዘመናት የተሰሩ ስህተቶች የሚታረሙበትና የወጣቱን ትውልድ ፍላጎትና ጥቅም ለማሳካት ትኩረት የሚደረግበት ይሆናል ብለዋል፡፡

ከለውጡ ዋዜማ ጀምሮ አገራችንን ወጥረው ከያዟት ችግሮች መካከል ዋናው ውስጣዊ አለመረጋጋት እንደሆነና ይህንንም ተከትሎ በየቦታው ያጋጠመው መፈናቀል በታሪካችን ጥቁር ጠባሳ ጥሎ ያለፈ እንደሆነም  አንስተዋል፡፡

የደህንነትና የጸጥታ ተቋማት የሚያጋጥሙ ችግሮችን ቀድመው የማወቅና ሲከሰቱም በአጭር ጊዜ የማስቆም ብቃታቸውን በማጎልበት እንደነዚህ አይነት ክስተቶች ዳግም እንዳይፈጠሩ ለማድረግ የሚያስችሉ ስራዎች ትኩረት ይሰጣቸዋል ብለዋል፡፡

“ሠላም በእያንዳንዳችን እጅና ልቦና ውስጥ የሚገኝ ውድ ሃብት ነው” ያሉት ፕሬዘዳንቷ በመሆኑም ይህንን ውድ ሃብት ልንከባከበውና በእጃችን የሚኖር ሃብት ሆኖ እንዲቀጥል ጠንክረን መስራት ይጠበቅብናል በማለት አሳስበዋል፡፡

ህዝቡ ከተለያየ ቦታና አጋጣሚ በሚነዙ አሉባልታዎች ሊፈተንና አርቆ አስተዋይነቱ ሊሸረሸር እንደማይገባም አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡

መንግስት የተጣለበትን የህግ ማስከበር ሃላፊነት ከመወጣት ጎን ለጎን የመረጃ ተደራሽነትን ለማስፋት ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራም ፕሬዘዳንቷ አክለው ገልጸዋል፡፡