null The fourth public and house census was extended for the second time.

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የህዝብ ተወካዮችና የፌደሬሽን ም/ቤቶች 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ ልዩ የጋራ ስብሰባ ሰኔ 3 ቀን 2011 ዓ.ም አካሂደዋል፡፡

በአገራችን በየአስር ዓመቱ የሚካሄደውን የህዝብና ቤቶች ቆጠራ ለማከናወን ሰፊ የሰው ሀይል፣ የሀብት ምደባና የመሳሰሉት ቅድመ ዝግጅቶችን በጥንቃቄና በአግባቡ መምራትን የሚጠይቅ ትልቅ አገራዊ ጉዳይ እንደሆነ የገለጹት የሁለቱም ም/ቤት አፈጉባኤዎች ከዚህ አኳያ በያዝነው በጀት አመት ይካሄድ ነበረውን የህዝብና ቤቶች ማራዘም ማስፈለጉን አስረድተዋል፡፡

የህዝብና ቤቶች ቆጠራ ውጤት ለአገራቱ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ባህላዊ የልማት እቅዶች፣ ፕሮግራሞች፣ ፖሊሲ ሃሳቦች፣ ሀብት በፍትሃዊነት ለመመደብና ለማስተዳደር ተጨባጭ ሳይንሳዊ የመረጃ ምንጭ በመሆን የሚያገለግል እንደሆነ የተከበሩ አቶ ታደሰ ጫፎ አስገንዝበዋል፡፡

በአገራችን ላለፉት ወራት በተለያዩ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ምክንያቶች ተነሳ የህዝብ ቆጠራን በሳይንሳዊ መንገድ ለማካሄድና ለመምራት የማያስችሉ ሁኔታዎች በመፈጠራቸው የተሻለ ምቹ ሁኔታ እስኪፈጠር ቆጠራውን ለማካሄድ ሀላፊነት የተሰጠው ኮሚሽን በርካታ ጥናቶችን ሲያካሂድ መቆየቱንም አፈ ጉባኤበው በዝርዝር አስረድተዋል፡፡

አቶ ታገሰ አክለውም በአገራችን የሚካሄደው የህዝብና ቤት ቆጠራ በተረጋጋና ምቹ ህሊናዊና አካባቢያዊ ሁኔታ መካሄድ አማራጭ የሌለውና የሁሉንም የአገሪቷ ህዝቦች የሚጠቅም ጉዳይ እንደመሆኑ መጠን የህዝብን ዘላቂ ጥቅም በሚያረጋግጥ መንገድ ቆጠራውን ማካሄድ አስፈላጊ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

የሁለቱም ምክር ቤቶች አባላት በውሳኔ ሀሳቡ ላይ በዝረዝር ከተወያዩና ከተከራከሩ በኋላ የቆጠራው መራዘም ዋና ዓላማ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በተለያዩ አካባቢዎች እየተፈናቀሉ ስለሆነ እነሱን ወደ ቀያቸው የመመለስ ስራው ቅድሚያ ሊሰጠው እንደሚገባ አስታውሰው በሌላ በኩል ደግሞ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እየተመለሱና እየመጡ ስለሆነ የሰላም ሚኒስተርም እስከ ሰኔ 30/2011 ዓ.ም እንደሚመለሱ ስለገለጸ ምርጫው መራዘም የለበትም የሚሉ የምክር ቤት አባላትም ሀሳባቸውን አንስተዋል፡፡

የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ በበኩላቸው ቆጠራውን ለማካሄድ የተለያዩ ዝግጅቶችና ቁሳቁሶች የተሟሉ ቢሆኑም የህዝብና ቤት ቆጠራውን ለማካሄድ የሚያስችል ነባራዊ ሁኔታ እንደሌለና ከአገርና ህዝብ የሚበልጥ ጉዳይ እንደሌለ አስረድተው ከወጭ አንጻርም የሚጎዳ ነገር አለመኖሩን አስገንዝበዋል፡፡

በመጨረሻም ቆጠራው መቸ እንደሚካሄድ ለአንድ ዓመት ወይም የህዝብና ቤት ቆጠራ ኮሚሽን በሚያከናውናቸው ስራዎች እንደ ሁኔታው እየታየ ላልታወቀ ጊዜ ይራዘም የሚሉ በርካታ ክርክሮች ተነስተው ለአንድ ዓመት እንዲራዘም በ30 ተቃውሞ፣ በ3 ተዓቅቦና በአብላጫ ድምጽ 4ኛው የህዝብና ቤት ቆጠራ ለአንድ ዓመት ተራዝሟል፡፡