null The government believes that the creation and continuation of a peaceful and stable country calls for the presence of a democratic system.

መንግስት ሰላምና የተረጋጋ ሃገር ለመፍጠር የሚያስችል የዴሞክራሲ ስርዓት ለመገንባት   ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል ሲሉ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ.ፕሬዘዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ተናገሩ፣

5ኛው የህዝብ ተወካዮችና የፌደሬሽን ምክር ቤቶች 4ኛ አመት የስራ ዘመን 1ኛ አመት የጋራ መክፈቻ ስነ-ስርዓት ተካሄደ፡፡

በስነ-ስርዓቱ ላይ ተገኝተው  የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ፕሬዘዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ በባለፈው አንድ አመት የመንግስታቸው አፈጻጸምና ወደ ፊት ሊተኮርባቸው ይገባል ባሏቸው ጉዳዮች ላይ መለዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ሰላምና የተረጋጋ አገር መገንባት የሚቻለው የዴሞክራሲ ስርዓት ሲፈጠርና ጽኑ መሰረት ሲኖረው ነው ያሉት ፕሬዘዳንቱ ከዚህ አኳያ ወቅቱ የፍትህና የዴሞክራሲያዊ ስርዓቱን በማበልጸግ ረገድ ቁልፍ ሚና የሚኖራቸውን ህጎች፣ ተቋማትና አሰራሮችን ለይቶ ተገቢውን የማሻሻያ እርምጃ የምንወስድበት ነው ብለዋል፡፡

መንግስት የአገራችን ህዝቦች የአብሮነትና የመቻቻል አይነተኛ እሴት የሆነውን ሃብት ለመናድ የሚደረገውን መረን የለቀቀ ስርዓት አልበኝነት ላይ ልዩ ትኩረት በመስጠት የእያንዳንዱን ዜጋ ደህንነትና ነፃነት ለማስከበር አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ ሁሉ እንደሚቀስድ ፕሬዘዳንቱ አስታውቀዋል፡፡

የዴሞክራሲ ምህዳሩን ለማስፋት የተጀመረው የሪፎርም ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የጠቆሙት ፕሬዘዳንቱ የዴሞክራሲ ስርዓቱ እንዲጎለብትና ያሉት መልካም ጅምሮች ተቋማዊ ቅርጽ ይዘው እንዲቀትሉ የህግ ማዕቀፉን ማሻሻልና የዴሞክራሲ ተቋማትን ማጠናከር ብቸኛው አማራጭ ነው ብለዋል፡፡

የምርጫ ህጉ ስልጣን በሃይል ለማያዝ ከሚደረግ አዞሪት ወጥተን ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር በመመካከር ሰላማዊና የሰለጠነ አካሄድን የተከተለ እንዲሆን ለማድረግ በመንግስት በኩል ቁርጠኝነት መኖሩን ያነሱት ፕሬዘዳንቱ ተፎካካሪ ፓርቲዎችም ሃገራችንን ወደፊት ሊያራምዳት በሚችለው የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ላይ በሃላፊነት መንፈስና ህግን በተከተለ አካሄድ የበኩላቸውን አስተዋጽ ሊያደርጉ ይገባል ሲሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በኢኮኖሚው ዘርፍ በተያዘው በጀት አመት የልማታዊና ዴሞክራሲያዊ ነፃ ገበያ ስርዓትን በመገንባት የተረጋጋ ማይክሮ ኢኮኖሚ ለማረጋገጥና ማህበረ-ኢኮኖሚ ልማትን ለማበረታት መንግስት አበክሮ ይሰራል ያሉት ፕሬዘዳንቱ በታክስ ገቢ አሰባሰቡም ላይ ትኩረት ይደረጋል ብለዋል፡፡

የብድር አስተዳደሩንና አጠቃቀሙን ውጤታማ ለማድረግ እና የመንግስት ፋይናንስ ከመንግስት ሴክተር ውጪ የሆኑ ኢንቨስትመንቶችን ለማሳደግ በሚያስችል ሁኔታ አሰራሩ ይሻሻላልም ተብሏል፡፡