null The House Decided the highest court Judge Ayele Dibo to return to work.

የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ አየለ ዲቦ ወደ ስራ ገበታቸው እንዲመለሱ ምክር ቤቱ ወስኗል፤

ግንቦት 13 ቀን 2011 .ም፤ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአካሄደው 40 መደበኛ ስብሰባው የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ አቶ አየለ ዲቦ ፈፀሙት በተባለ ከባድ የዲሲፕሊን ጥፋት ከዳኝነት ስራቸው እንዲሰናበቱ የፌደራል የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ያቀረበውን ውሳኔ አስመልክቶ በህግ፤ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የቀረበለትን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ አድምጧል፤

ዳኛው የክስ ይጣመርልኝ አቤቱታ በአራዳ ምድብ ችሎት ቀርቦ የተከለከለ መሆኑንና ለከፍተኛው ፍርድ ቤት አቤቱታ ቀርቦ ተቀባይነት ማጣቱን አላወኩም ብለው የሰጡት መልስ አግባብነት የሌለው እና ማረጋገጥ ነበረባቸው በሚል በአቻ ፍርድ ቤት የተሰጠን ትዕዛዝ መጣሳቸው ተነስቷል፤

ምክር ቤቱ በቋሚ ኮሚቴው የቀረበለትን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ አድምጦ ከመረመረ በኋላ፤ ዳኛው ከዚህ በፊት በሙያቸው የተመሰገኑ፤ የስነ- ምግባር ችግር የሌለባቸው እና የመጀመርያ ስህተታቸው ነው የሚለው የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ አባላት የልዩነት ድምፅ ግምት ውስጥ በማስገባት ከማባረር በመለስ በውሳኔ ሃሳቡ ላይ የተገለፀው ስህተት የሚመጥን የዲሲፕሊን ቅጣት በዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ደንብ መሰረት ተቀጥተው ወደ ስራ ገበታቸው እንዲመለሱ በስምንት ተቃውሞና በአምስት ተዓቅቦ በአብላጫ ድምጽ የውሳኔ ሃሳቡን ምክር ቤቱ አፅድቆታል፡፡

ምክር ቤቱ የነዳጅና የነዳጅ ውጤቶች አቅርቦትና ተቆጣጣሪ ባለስልጣን ማቋቋሚያ አዋጅ አጽድቋል፡፡

ምክር ቤቱ በአዋጁ አንዳንድ አንቀጾች ላይ በዝርዝር ተወያይቷል፤ ተከራክሯል፤ ምክር ቤቱ በተናጠል ድምጽ ከሰጠ በኋላ አዋጁን በአብላጫ ድምጽና በአንድ ድምፀ ተዓቅቦ አጽድቆታል፡፡

የነዳጅና የነዳጅ ውጤቶችን አቅርቦትና ስርጭት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፉ ለማድረግ የአሰራር ስርዓትን መዘርጋት የሚያስችልና የመጠባበቂያ ክምችት መጠን በአይነት እንዲወሰን የክምችት አስተዳደር ስራ በሚገባ እንዲመራ ተቆጣጣሪ ባለስልጣን ማቋቋም አስፈላጊ መሆኑን የንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ጌታቸው መለሰ ገልጸዋል፡፡

ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ማቋቋሚያ አዋጅን ለማስፈጸም የቀረበ ረቂቅ ደንብ ላይ ከተወያየ በኋላ ለዝርዝር ዕይታ ለህግ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መርቷል፡፡