null The House endorses agreement bill.

ጥቅምት 27 ቀን 2011 ..፤ አምስተኛ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 6ተኛ መደበኛ ስብሰባው በኢትዮጵያ መንግስት እና በአለም አቀፍ የልማት ማህበር መካከል ለተወዳዳሪነት እና ስራ ፈጠራ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የአንድ መቶ ሰባ አምስት ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ተጨማሪ ብድር ስምምነት አጽድቋል፡፡

ምክር ቤቱ የብድር ስምምነቱን ያጸደቀው የበጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ በተመለከተ ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ   መሠረት አድርጎ ነው፡፡

ከአለም አቀፍ የልማት ማህበር የተገኘው አንድ መቶ ሰባ አምስት ሚሊዮን ዶላር ተጨማሪ ብድር የቦሌ ለሚ 2 እና የቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ግንባታ ቆይታ በማሳጠር በተሻለ ጥራት የሚያስጨርስ መሆኑን  ተጠቅሶ  የኢንዱስትሪው ዘርፍ  በኢኮኖሚ ውስጥ የመሪነት ሚናውን እንዲረከብ መንግስት የሚያደርገውን ጥረት በመደገፍ እየተመዘገበ ያለውን ፈጣን የኢኮኖሚ ዕደገት ለማስቀጠልና ለኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን መሰረት ለመጣል አጋዥ በመሆኑ  እንደሆነ የበጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ነጋልኝ ዮሴፍ  ገልጸዋል፡፡

ተጨማሪ ብድሩ ወለድ የማይከፈልበት ሲሆን 6 ዓመት የችሮታ ጊዜን ጨምሮ  38 ዓመታት ውስጥ ተከፍሎ  እንደሚያልቅ ለማወቅ ተችሏል፡፡  በሌላ በኩል ባንኩ የብድሩን ገንዘብ በማስተዳደር ለሚሰጠው አገልግሎት እንዲውል እና ባልተከፈለው ገንዘብ ላይ በየዓመቱ 0.75% የአገልግሎት ክፍያ ባንኩ በሚወስነው መሰረት ጥቅም ላይ ባልዋለው የብድር ገንዘብ ላይ በዓመት 0.50% የሚደርስ የግዴታ ክፍያ ሊከፈልበት የሚችል እንደሆነና ብድሩ  ከሃገራችን የብድር አስተዳደር ስትራቴጂ ጋር የተጣጣመና ጫናው ያልበዛ መሆኑንም አብራርተዋል፡፡

ብድሩ ፕሮጀክቱን የተሟላ በማድረግ የውጭ ኢንቨስተሮችን በመሳብ ከተወዳዳሪነትና የስራ ፈጠራ በተዛማጅ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማትን ለማስፋፋትና የኢንቨስትመንት ወጪ ለመቀነስ እንዲሁም አገልግሎቶችን በተሻለ ቅልጥፍና ለማቅረብ የሚያግዝ  እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

በተጨማሪም ኢንዱስትሪዎች በመደጋገፍ በእሴት ሰንሰለት የሚተሳሰሩበትን እድል ስለሚፈጥር የግሉ ዘርፍ በኢኮኖሚው ውስጥ ተገቢውን ሚና እንዲጫወት እና አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች በሚፈጠረው የኢኮኖሚ ትስስር ተጠቃሚ ሆነው ለድህነት ቅነሳና ለስራ ዕድል ፈጠራ አስተዋጽኦ  የሚያበረክት መሆኑንም የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሪፖርቱን ባቀረቡበት ወቅትልጸዋል፡፡

ምክር ቤቱ 4ተኛ አመት የስራ ዘመን 5ተኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ ጉባኤም መርምሮ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡