null The House has also been able to speed up the country's reform process.

ምክር ቤቱ በህግ አወጣጥ ሂደት እያከናወናቸው ያሉ ተግባራት የተጀመረውን ሃገራዊ ሪፎርም ለማስቀጠልና ለማፋጠን የሚያስችሉ መሆናቸው ተገለፀ፤

ግንቦት 9/211 የህዝብ ተወካዮች የም/ቤቱ /ቤት ዋና ፀሃፊ / ምስራቅ መኮንን የም/ቤቱን የሚያዚያ ወር የሥራ አፈፃፀምን አስመልከተው ዛሬለጋ ዜጠኞች መግለጫ ሠጥተዋል፡፡

የህዝብ ተወካዮች /ቤት ከቀረበለት 12 ረቂቅ አዋጆች መካከል 7ቱን ለሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች ለዝርዝር እንይታይ ሲመራ 5ቱን መርምሮ አፀድቋል፡፡

/ ምስራቅ በመግለጫቸው እንዳሉት /ቤቱ በዋናነት መደበኛ ጉባኤዎችን፣ በም/ቤት አባላት የተደረገ የመስክ ምልከታ፣ የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ ከአስፈፃሚ /ቤቶች ጋር ያደረገው የሥራ አፈፃፀም ግምገማ እንዲሁም የህግ አወጣጥ ሥራዎች ተጠቃሽ ናቸው፡፡

/ቤቱ ከቀረቡለት 12 ረቂቅ አዋጆች መካከል ፤ከሲዌዝ መንግስት ጋር የተፈረመ የአየር አገልግሎት ሥምምነት፣ የኢትዮ -ጅቡቲ የሁለትዮሽ የንግድ ስምምነት፣ የኢትዮ- ህንድ የሁለትዮሽ የንግድ ሥምምነት፣የህዝብ እንባ ጠባቂ አዋጅን ለማሻሻል የወጣ አዋጅ እና የምስራቅ አፍሪካ የክህሎት ሽግግር ኘሮጀክት ማስፈፀሚያ ከአለም አቀፍ የልማት ማህበር ጋር የተደረገ የብድር ሥምምነት አዋጅን አጽድቋል፡፡

የፀደቁት አዋጆች የተጀመረውን ሃገራዊ ሪፎርም ለማፋጠን እና ለማስቀጠል፣ የአካባቢውን ሠላም ለማረጋገጥ እንዲሁም ዜጐችን እኩል ተጠቃሚ ለማድረግያ ግዛሉ ተብሎ የታመነባቸው መሆኑንም / ምስራቅ በመግለጫቸው አንስተዋል፡፡

/ቤቱ ቀሪ 7 ረቂቅ አዋጆችን ለሚመለከታቸው የቋሚ ኮሚቴዎች ለዝርዝር እይታ መርቷል፡፡

ለቋሚ ኮሚቴ ከተመሩ ረቂቅ አዋጆች መካከል የጦር መሣሪያ አስተዳደርና ቁጥጥር፣ በተንቀሣቃሽ ንብረት ላይ ያለዋስትናመብት፣ የነዳጅና ነዳጅ ውጤቶች አቅርቦትና ሥርጭት፣ የማዕድን ግብይት አስተዳደር የፌዴራል ዋና ኦዶዲተር ማቋቋሚያ አዋጅ፣የኮሚኒኬሽን አገልግሎት እንዲሁም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ረቂቅ አዋጆች ናቸው፡፡

በክትትልና ቁጥጥር ስራም 6 የፌዴራል መንግስት ተቋማትን 9 ወር የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት በማድመጥ ምክር ቤቱ ገምግሟል፤ በሦስት ዩኒቨርስቲዎች፣በነጭ ሣር ብሔራዊ ፓርክ፣ በመድሃኒት ፈንድ እንዲሁም በኮንስትራክሽን ዘርፍ እና በቃሊቲ ጉምሩክ ኬላ በመገኘት የክትትልና የቁጥጥር ሥራዎች በወሩ በምክር ቤቱ አባላት ከተከናወኑ ተግባራት መካከል የሚጠቀሱት ናቸው፡፡

የፓርላማ ዲኘሎማሲን በተመለከተ ከዮናይትድ ኪንግደም የም/ቤት አባላት፣ ከሰርቪያ አምባሳደር፣ ከኒውዝላንድ አፈ ጉባኤ፣ ከአውስትራሊያ እና ከደቡብ አፍሪካ ሃገራት የጋራ /ቤቶች ትብብር ጋር ምክክር ተደርጓል፡፡እንዲሁም ኢትዮጵያ ከአለም አቀፉ የፓርላማ ማህበራት አባል በመሆኗ የጉባዔው ታዳሚ በመሆን የተሳተፈች በዚሁ በሚያዚያ ወር ነው፡፡

በተጨማሪም ምክር ቤቱ የቀረበለትን 3 የሚኒስትሮች ሹመት አፅድቋል፤ በሃገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች በተፈጠረው ግጭት ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጐችን መልሶ ለማቋቋምና ለመደገፍ /ቤቱ አቅጣጫ ማስቀመጡንም / ምስራቅ በመግለጫቸው አስታውሰዋል፡፡