null Membership training for members of the House was given to the conscientiousness and the achievement of work.

በህሊና ገዥነት እና ስራን ከዳር ማድረስ ላይ ለምክር አባላት ስልጠና ተሰጠ፡፡

ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላትና ለምክር ቤቱ ጽህፈት ቤት ሰራተኞች ጥራት ያለው ተግባር እንዲፈፅሙ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ የአንድ ቀን የስልጠና ግንቦት 9 ቀን 2011 . በታዋቂው የአዕምሮ ሀኪም ዶክተር ምህረት ደበበ አማካይነት ተሰጠ፡፡

ስልጠናው በህሊና ገዥነት እና ስራን ከማድረስ ላይ ያተኮረ ላይ ያተኮረ ነበረ፡፡ ህሊና የሞራል ዕውቀት ማዕከል ሆኖ ግለሰቡ ራሱን የሚመራበት አቅጣጫ ጠቋሚ ማሳሪያ ሆኖ በተፈጥሮ የሚያዝ ሆኖ በማህበረሰቡ እንደሚቀረፅ የገለፁት ዶክተሩ በጣም ጠቃሚ ሃሳብ በመሆኑ የምክር ቤት አባላት ጭምር እንዲገዛበት በህገ መንግስቱ መደንገጉን ጠቁመዋል፡፡

ህሊና ሰው ንፁህ ሆኖ እንዲገኝ፣ ሙሉዕ፣ ተገማች፣ ግልፅና የማያስመስል እንዲሆን እና ከራሱ ጋር የተጣላ እንዳሆን እንደሚያደርግ የገለፁት ዶክተሩ ከዚህ በተጨማሪ ሰው የጎረቤቱን ህሊና እንዲቃኝና ከሌሎች ጋር ህሊና ለህሊና እንዲናበብ ስለሚያስችል ይህም ለምክር ቤቱ ህግ አወጣጥ በጣም እንደሚጠቅም ነው ተንትነው ያስረዱት፡፡

የምክር ቤቱ አባላት ለሚወስኑት ውሳኔ እርስ በርሳቸው እንዲናበቡና ያወጡት ህግም የህዝቡን ህሊና እንዲገዛ ያስረዱት ምሁሩ ህዝቡን ያማከለ ህግ በህዝቡ እንደሚተገበርና ከህዝቡ ህሊና ውጭ የሆነ ህግ ለጥሰት እንደሚጋለጥ በምሳሌ በማስደገፍ ነው ያስረዱት፡፡

ህሊና መታመም የሚችል ቢሆንም በምክንያታዊነት፣ ስሜትን በመግዛት እና በዕምነት ፅናት ህመሙን መከላከል እንዲቻል ያመለከቱት ዶክተሩ ንፁህ ህሊና ሀሳብን፣ ቃልንና ድርጊትን በወጥነት እንዲጣመሩ በማድረግ ማግኘት እንደሚቻል ነው ያስተማሩት፡፡

የታመመ ህሊና የሚፀዳው በግል ራስን በመገምገም፣ ያሰቡትን በመናገር፣ ምክንያትንና ስሜትን ከዕምነት ጋር በማጣጣምና የሌሎች ሰዎችን ክብር፣ ድንበርና ንብረት በመጠበቅ እንደሆነም ዶክተር ምህረት አስረድተዋል፡፡ ምክር ቤት አባላት ህሊናን መጣስ እንደማይገባቸው ነው መልዕክት ያስተላለፉት፡፡

ሌላው ርዕስ ስራን መጨረስ ሲሆን የምክር ቤቱ አባላት ያፀደቁት በጀትና የፈቀዳቸው ፕሮጀክቶች በጥራት ተሰርተው በጊዜ እንዲጠናቀቁ ማንኛውንም ጫና ተቋቁመው እንዲጨርሱ መክረዋል፡፡ ሰበብና ምክንያት መደርደር ስራዎች እንዳያልቁ አድርገው በመጨረሻም ዋጋ እንደሚያስከፈሉ በምሳሌ አስረድተዋል፡፡

ህሊና የሚያርፈው የተጨረሰ ነገር ላይ መሆኑን በመጠቆም ዛሬ ያለቀ ነገር ነገ ጥሩ ታሪክ እንደሚሆን አክሱም ሃውልትንና የላሊበላን ውቅር ቤተክርስቲያን ለማሳያነት አቅርበዋል፡፡ በወቅቱ የነበሩ ነገስታት በቁርጠኝነት ሰርተው በማጠናቀቃቸው ለአገሪቱ ክብር ለውጭ ዜጎች ደግሞ የቱሪስት መዳረሻ ለመሆን መብቃቸውን በማስታወስ ፓርላማውም ይህን እንዲከተል መክረዋል፡፡

ለዚህ የመርህ ሰው መሆን፣ ሰው ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት፣ ስራውን ጠንቅቆ ማወቅና ጥራት እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል፡፡ የምክር ቤት አባላትም ህልውናና ህሊናን እንዴት ማጣጣም እንደሚቻል የጠየቁ ሲሆን ለህልውና ዋስትና የሚሆኑ ጉዳዮችን ለይቶ መፍታት እንደሚገባና ይህም በምክር ቤቱ እጅ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡