null The House in its 18th regular session referred a different bill to the concerned committee

ምክር ቤቱ በ18ኛ መደበኛ ሰብሰባው የተለያዩ ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ ለዝርዝር እይታ መርቷል፡፡

ጥር 2 ቀን 2011 ዓ.ም፤ 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በ4ኛ ዓመት የስራ ዘመኑ በአካሄደው 18ኛ መደበኛ ስብሰባው የቀረቡለትን የተለያዩ ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ ለሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች  ለዝርዝር  እይታ መርቷል፡፡

የሕገ መንግስትና የፌዴራሊዝም አስተምህሮ ማዕከልን ለማቋቋም የቀረበ ረቂቅ አዋጅ ቁጥር18/2011፣ የሲቪልማህበረሰብ ድርጅቶች ረቂቅ አዋጅ ቁጥር19/2011፣የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትን እንደገና ለማቋቋም የቀረበ ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 20/2011 ሆነው በሙሉ ድምጽ ለህግ፣ ፍትህ እና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለዝርዝር እይታ ተመርተዋል፡፡ እንዲሁም በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት እና በአልጄሪያ ሕዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት መካከል በእንስሳት እና አሳ እርባታ ዘርፍ የተደረገውን ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበ ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 21/2011 ሆኖ በዋናነት  ለውጭ  ግንኙነትና  ሠላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በተባባሪነት ደግሞ ለግብርና፣ አርብቶ አደር እና አካባቢ ጥበቃ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሙሉ ድምጽ የተመራ ሲሆን፤በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት እና በአልጄሪያ ሕዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት መካከል የተደረገውን የሁለትዮሽ የንግድ ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበ ረቂቅ አዋጅ  ቁጥር 22/2011 ሆኖ በሙሉ ድምጽ በዋናናት ለውጭ ግንኙነትና ሠላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ  በተባባሪነት ለንግድና ኢንዱስትሪ ቋሚ ኮሚቴ  ምክር ቤቱ ለዝርዝር እይታ መርቷል፡፡

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሰት እና በአልጄሪያ ሕዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት መካከል በእጽዋት ማቆያ እና ጥበቃ ዘርፍ የተደረገውን ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበ ረቂቅ አዋጅ መርምሮ በዋናነት ለውጭ ግንኙነትና ለሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በተባባሪነት ለግብርና፣አርብቶ አደርና አካባቢ ጥበቃ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሙሉ ድምጽ የመራ ሲሆን፤  በሁለቱ መንግስታት መካከል በኮሙኒኬሽን እና ኢንፎርሜሽን ዘርፍ ለመተባበር የተፈረመውን ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ መርምሮ በዋናነት ለውጭ ግንኙነትና ለሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በተባባሪነት ለህግ፣ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሙሉ ድምጽ መርቷል፡፡

በተመሳሳይ ምክር ቤቱ በኢትዮጵያ መንግስትና በኳታር መንግስት መካከል  የዲፕሎማቲክ ወይም ሰርቪስ/ልዩ ፓስፖርቶች ለያዙ ሰዎች ቪዛን  ለማስቀረት የተፈረመውን ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበ ረቂቅ አዋጅ መርምሮ ለውጭ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሙሉ ድምጽ መርቷል፡፡

በመጨረሻም ምክር ቤቱ በዛሬው ውሎው በሁለቱ መንግስታት መካከል የተፈረመውን የአጠቃላይ ትምህርት፣የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና የሳይንሳዊ ምርምር ዘርፍ ትብብር የመግቢያ ሰነድ ለማጽደቅ የቀረበውን ረቂቅ አዋጅም መርምሮ በዋናነት ለውጭ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እና በተባባሪነት ለሰው ሃብት ልማትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ  በሙሉ ድምጽ መርቷል፡፡