null The House in its 27th regular session held on 14th Mar.2019, referred three agreement draft bills for concerned committees.

ምክር ቤቱ በ27ኛ መደበኛ ስብሰባው ሶስት የብድር ስምምነቶችን ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ  ለዝርዝር እይታ መርቷል፡፡

መጋቢት 5 ቀን  2011 ዓ.ም፤ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 27ኛ መደበኛ ስብሰባው፤3 የብድር ስምምነቶችን መርምሮ ለገቢዎች፣በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የመራ ሲሆን፤ ከነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት እና በቻይና ኤክስፖርት-ኢምፖርት ባንክ መካከል ለመቀሌ ውሃ አገልግሎት አቅርቦት ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ ለማጽደቅ የቀረበ ረቂቅ አዋጅ አንዱ ነው፤ ረቂቅ አዋጁ  በ4 ተቃውሞ እና በ16 ድምፅ ታቅቦ በአብላጫ ድምፅ ነው ምክር ቤቱ ለሚመለከተው ኮሚቴ የመራው፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ረቂቅ አዋጅን ለማሻሻል የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ ምክር ቤቱ በዝርዝር ከተወያየበት በኋላ ረቂቅ አዋጅ 44/2011 ሆኖ ለዝርዝር እይታ ለሰው ሃብት ልማት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሞ ኮሚቴ በሙሉ ድምጽ የመራ ሲሆን፤ ጥራት ያለው እና   ብቁ ትውልድ የሚቀርጽ ህግ ለማውጣት የተመራለት ቋሚ ኮሚቴ የረቂቅ አዋጁን ዋና ዋና   ድንጋጌዎች በጥልቀት እንዲመረምር እና አለም አቀፍ ተሞክሮዎችንም እንዲያጤን ምክር ቤቱ አመላክቷል፡፡

በዚሁ የምክር ቤቱ መደበኛ ስብሰባ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት እና በህንድ ሪፐብሊክ መንግስት መካከል የሁለትዮሽ የንግድ ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ ረቂቅ አዋጅ  ቁጥር 46/2011 ሆኖ በዋናነት ለውጭ ግንኙነት እና ለሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በተባባሪነት ለንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሙሉ ድምጽ ተመርቷል፡፡

ምክር ቤቱ የህገ መንግስት እና የፌደራሊዝም አስተምህሮ ማእከልን ለማቋቋም የቀረበ የረቂቅ አዋጅ ሪፖርት እና የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ   በሶስት ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ አጽድቆታል፡፡

የምክር ቤቱ የ4ኛ አመት የስራ ዘመን 26ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ ጉባኤም  በሙሉ ድምፅ ፀድቋል፡፡