null The House in its 44th regular session approved the appointment of the National Electoral Board members.

ምክር ቤቱ ባካሄደው 44ኛ መደበኛ ስብሰባ የቀረበለትን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አባላትን ሹመት መርምሮ አጸደቀ፣

ምክር ቤቱ ተንቀሳቃሽ ንብረትን የብድር ዋስትና ለማስያዝ የሚያስችል፣ ሴቶችን በንግድ ዘርፍ ተጠቃሚ ለሚያደርጉ ፕሮግራሞች ማስፈጸሚያ የሚውል የብድር ስምምነትን እና ሌሎች የውሳኔ ሃሳቦችን መርምሮ አጽድቋል፡፡  

ም/ቤቱ ሰኔ 6 ቀን 2011 ዓ.ም ባካሄደው 44ኛ መደበኛ ስብሰባ  የምርጫ ቦርድ አባላትን ሹመት፣ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዕጩ ዳኞችን፣ ፌዴደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትና ፌዴደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዕጩ ፕሬዝዳንት ሹመት እና አራት የቀረቡ የተለያዩ የውሳኔ ሃሳቦችን መርምሮ ሲያጸድቅ የኢትዮጵያ ተወላጆች የሆኑ የውጭ ዜጎችን በባንክ ስራ ላይ ተሳታፊ የሚያደርግ አዋጅ ለማሻሻል የቀረበለትን ረቂቅ አዋጅ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መርቷል፡፡

በጠ/ሚ የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ ያቀረቡት ረዳት የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት መንግስት ነጻ፣ ትክክለኛ እና በህብረተሰቡ ዘንድ ተዓማንነት ያለውን ምርጫን ለማከሄድ የሚችል ገለልተኛና ብቃት ያለው ምርጫ ቦርድ ለማቋቋም ባለው ሃላፊነትና የፖለቲካ ቁርጠኝነት ይህንን አገራዊ ሃላፊነት ለመወጣት የሚችሉ ምርጫ ቦርድ አባላትን በእጩነት ማቅረቡን አስረድተዋል፡፡

በዚህም መሰረት ወ/ሪት ብዙወርቅ ከተተ፣ አቶ ውብሸት አየለ፣ ዶ/ር ጌታሁን ካሳ እና ረዳት ፕ/ር አበራ ደገፋ ነጋዎን የሾመ ሲሆን አቶ ውብሸት አየለ በምክትል ሰብሳቢነት እና በወቅቱ የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው እያገለገሉ እደሚገኙም ገልጸው የቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ቁጥር 28/2011 ሆኖ በ17 ተቃውሞ በአንድ ድምጸ ታቅቦ በአብላጫ ድምጽ ጸድቋል፡፡

የም/ቤቱ አባላትም የተለያዩ አስተያየቶችን የሰጡ ሲሆን የተደረገው ምልመላ ብቃትን መሰረት ያደረገ ነው ቢባልም በተቃራኒው ከዚህ በፊት የሚደረገው ምልመላ ከአራቱ ብሔራዊ ድርጅቶች ውጭ የአጋር ድርጅቶች ተሳትፎ ያለበት እንደነበር ነገር ግን የዘንድሮ ለምን አላካተተም ሲሉ ጠይቀው አምባሳደር መስፍን በምላሻቸው የተደረገው ምልመላ አሁን ላይ እየመጣ ያለውን ለውጥ ከግምት ውስጥ ያስገባ እና በተለይ በልምድ እንዲሁም የትምህርት ዝግጅትን ታሳቢ ያደረገ ሆኖ ሁሉንም የህብረተሰብና ፓርቲዎችን ያቀፈ እንደሆነ ነው ያስገነዘቡት፡፡

ም/ቤቱ በውሎው የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ያቀረባቸውን በህግ ትምህርት የሰለጠኑ ወይም በልምድ በቂ የህግ ዕውቀት ያላቸው በታታሪነት፣ በፍትሐዊነት፣ በስነ-ምግባር መልካም ስም ያተረፉ፣ በሙያውም ለማገልገል ፍቃደኛ የሆኑ ዕጩ 16 የፌዴራል ፍርድ ቤት ዳኞችን ጨምሮ አቶ ብርሃነመስቀል ዋቅጋሪ ኢትቻ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት፣ ወ/ሮ ተናኜ ጥላሁን ቀጸላ እና አቶ ተክሊት ይመስል ባለኪ ምክትል ፕሬዝዳንት በማድረግ እንዲሁም አቶ ፉዓድ ኪያር አህመድ ለፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት፣ ወ/ሮ አሸነፈች አበበ አልቤ እና አቶ ተስፋዬ ንዋይ እንግዳሸት ምክትል ፕሬዝዳንት በማድረግ የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ ቁጥር 29/2011 ሆኖ በአስር ታቅቦ በአንድ ተቃውሞ በአብላጫ ድምጽ አጽቋል፡፡

ሌላኛው በውሎው ከታዩት ጉዳች ከዚህ በፊት አዋጅ ቁጥር 39/2011 ሆኖ በዋናነት ለሰው ሃብትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴና በተባባሪነት ለንግድና ኢኒዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የለዝርዝር ዕይታ የተመራው የመንግስት የልማት ድርጅቶችን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ወደ ግል ለማዘዋወር በተያዘው አቅጣጫ መሰረት የቴሌኮሚኒኬሽን አገልግሎት ወደ ግል ሲተላለፍ ጠንካራ ተቆጣጣሪ ተቋም የሆነውን የኮሙኒኬሽን ባለስልጣን እንዲቋቋም በማድረግ ዘርፉ የግል ባለሀብቱ ገብቶ ተወዳዳሪና ጥራት ያለው ለማድረግ ብሎም የልማት ተቋማት ተገቢውን ካሳ እንዲያገኙ የሚያስገድድ ሲሆን ም/ቤቱም በቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ላይ የተለያዩ ሃሳቦችን በማንሳት የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 1148/2011 ሆኖ በ3 ድምጸ ተአቅቦና በአብላጫ ድምጽ ጸድቋል፡፡

ከአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ በብድር የተገኘውን 30 ሚሊዮን ዩሮ በተለይ የሴቶችን ተጠቃሚነት በማጎልበት የስራ ዕድል ፈጠራ ፕሮጀክቶችን ለማጠናከር የሚውል ሲሆን ብድሩም አነስተኛና የረጅም ጊዜ ወለድ ያለው በመሆኑ ም/ቤቱም የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ በሙሉ ድምጽ ውሳኔ ሃሳብ ቁጥር 1149/2011 አድርጎ አጽድቋል፡፡

የብዙ ዜጎች ጥያቄና ፍላጎት ሊያሟላ የሚችል በተለይ ዝቅተኛ ገቢ ያለው የህብረተሰብ ክፍልን በግብርና፣ በንግድ፣ በአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንቨስትመንት ዘርፍ ላይ እንዲሳተፍ እንዲሁም ተጨማሪ የስራ ዕድል በመፍጠር ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያችል ተንቀሳቃሽ ንብረትን ለብድር የዋስትና መብት ማስያዝ የሚያስችለውን ረቂቅ አዋጅም በአንድ ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ አዋጅ ቁጥር 1147/2011 ሆኖ ጸድቋል፡፡

በመጨረሻም ም/ቤቱ ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆኑ የውጭ ዜጎች በባንክ ስራ እንዳይሳተፉ ሲያደርግ የነበረውን የባንክ ስራ ምቹና ቀልጣፋ ለማድረግ የሚያግዝ አሰራርን ለመዘርጋት የሚያስችለውን ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅም ቁጥር 64/2011 አድርጎ በሙሉ ድምጽ ለዝርዝር ዕይታ ለገቢ፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መርቷል፡፡