null The House refered different draft bills for different concerned committees.

ምክር ቤቱ የአሰሪና ሰራተኛ ረቂቅ አዋጅን ጨምሮ የተለያዩ ረቂቅ አዋጆች ላይ ተወያይቶ ለዝርዝር ምርመራ ለተለያዩ ቋሚ ኮሚቴዎች መራ፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ግንቦት 8 ቀን 2011 . ባደረገው 39 መደበኛ ስብሰባው በአራት ረቂቅ ህጎች ላይ ተወያይቷል፡፡ አንዱ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጽህፈት ቤት የሰራተኞች አስተዳደር ረቂቅ ደንብ፣ ሌላው የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ ማሻሻያ፣ የአሰሪና ሰራተኛ እና የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትን እንደገና ለማቋቋም የቀረቡ ረቂቅ አዋጆች ናቸው፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጽህፈት ቤት የሰራተኞች አስተዳደር ረቂቅ ደንብ የቀረበው ለምክር ቤቱ የሚሰጠው ሙያዊ ድጋፍና አስተዳደራዊ አገልግሎት ምክር ቤቱ አሁን ከደረሰበት ደረጃ ጋር እንዲመጥን ለማስቻል የወጣውን አዋጅ ለማስፈፀም የቀረበ ነው፡፡ አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ ረቂቅ ደንቡ ስለያዛቸው ጉዳዮች ለውይይት መነሻ እንዲሆን ከጠቆሙ በሗላ አንዳንድ የምክር ቤቱ አባላት በሰው ሀብት ልማት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሊታዩ የሚገባቸውን ጉዳዮች በማመልከት ረቂቅ ደንቡን ለዚህ ቋሚ ኮሚቴ መርቶታል፡፡

የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ የቀረበው ሀገሪቱን ለንግድ ስራ መጀመር ምቹ እንድትሆን ለማድረግና የአገልግሎት አሰጣጡን በቴክኖሎጂ በመደገፍ ተደራሽ ለማድረግ እንደሆነ ከቀረበው ሰነድ ለመገንዘብ ተችሏል፡፡ አንድ የምክር ቤቱ አባል የንግድ ምዝገባና ፈቃድ ህግ በተደጋጋሚ በምክር ቤቱ እየተሻሻለ መምጣቱን በመጠቆም የንግዱ ማህበረሰብ ምን ያህል በአሁኑ ረቂቅ አዋጅ ላይ እንደተወያየ እንዲታይ አስተያየት አቅርበዋል፡፡ ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 54/2011 ሆኖ ለንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለዝርዝር ምርመራ ተመርቷል፡፡

የአሰሪና ሰራተኛ ረቂቅ አዋጅ ሶስተኛው ሲሆን ማሻሻያው ህጉን ወቅታዊ ለማድረግ እንደሆነ ከመንግስት ረዳት ተጠሪ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት በኩል የተጠቆመ ሲሆን የተከበሩ ግርማ መኮንን(/) የወልድ ፈቃድ አሰጣጥ ላይ ትኩረት እንዲሰጥ አሳስበው ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 55/2011 ሆኖ በዋናነት ለሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እና በተባባሪነት ለህግ፣ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተመርቷል፡፡

የመጨረሻው የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትን እንደገና ለማቋቋም የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ሲሆን ማሻሻያው በድርጅቱ ሰራተኞች መካከል በቦርድና በሲቪል ሰርቪስ የነበረውን የአስተዳደር ልዩነት እንደሚያስቀር፤ ፕሬስ የህትመት ችግርን እንደሚቀርፍና የኤሌክትሮኒክ ህትመት እንዲጀምር ህጉ ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥርለት በውይይቱ ወቅት ተነስቷል፡፡ ከውይይቱ በሗላ ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 56/2011 ሆኖ ለህግ፣ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለዝርዝር ምርመራ ተመርቷል፡፡