null The House referred different bills to the concerned Standing Committees, including the defense of terrorism, the establishment of developmental institutions and the beneficiaries.

ም/ቤቱ ሽብርተኝነትን ለመከላከል የሚያስችል፣ የልማት ተነሺዎችን ለማቋቋም እንዲሁም ተጠቃሚ የሚያደርግን አዋጆች ጨምሮ ሌሎችን ለቋሚ ኮሚቴዎች መርቷል፡፡

ግንቦት 29 ቀን 2011 ዓ.ም ም/ቤቱ ባደረገው አራተኛ የስራ ዘመን 42ኛ መደበኛ ስብሰባ ስድስት አጀንዳዎችን መርምሮ ለቋሚ ኮሚቴዎች መርቷል፡፡

አጀንዳው ቀዳሚ ያደረገው በዓለም ሰላም ላይ እና ደህንነት ላይ ከፍተኛ ስጋት ከሆኑ ወንጀሎች አንዱ የሆነውን የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ያሚያስችል እንዲሁም ባለፉት ጊዜያት ተግባራዊ የሆነውን ሽብርተኝነትን በገንዘብ መደገፍን ጭምር ለመቆጣጠር ጭምር ሲሆን አዋጁም አላማ ያደረገው የሽብር ፈጻሚዎችን በህግ ተጠያቂ ለማድረግና ተመጣጣኝ ቅጣት እንዲያገኙ፣ ተጎጂዎች መልሶ ለማቋቋም የህክምና አገልግሎት እንዲገኙ የሚያስችል እና የመንግስትንና የህዝብን ደህንነት ለማረጋገጥ ሰብዓዊና ዲሞክራሲ መብቶች በአግባቡ እንዲጠበቁ ለማስቻል እንደሆነ በሪፖርቱ ላይ ተመላክቷል፡፡     

ም/ቤቱ በማሻሻያ አዋጁ ላይ በተብራሩ ህጎች በተለይ በ2001 የወጣው የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ ህረትሰቡን ያላሳተፈ፣ የዜጎችን መብትና ነጻነት አላግባብ ይገድባል እንዲሁም መንግስት ህጉን የፖለቲካ ዓላማ ለማሳካት አመቺ ሁኔታዎችን የሚፈጥር ነው በመባል ከፍተኛ ቅሬታ ብሎም ትችት ሲቀርብበት እንደነበረ አስተውሶ የዜጎችን መብትና ነጻነቶችን ላይ አላአግባብ ገደብ የሚያደርጉ ህጎች በተገቢው መንገድ የሚፈጸምበት ሂደትን ያካተተ እንዲሆን እንዲታይ የቀረበው ረቂቅ አዋጁን አዋጅ ቁጥር 57/2011 ሆኖ በዋናነት ለህግ ፍትህና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እና በተባባሪነት ለውጭ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሙሉ ድምፅ መርቷል፡፡

አገራችን ኢኮኖሚው ከሚያመነጨው ሀብት አንፃር ሊያገኝ ይችል የነበረውን ገቢ ካላስገኘው ከታክስ ማጭበርበር፣ የተንዛዛ የታክስ አስተዳደር ስርዓት እና መሰል የንግድ ስራን እንዳይቀላጠፍ በማድረግ ከፍተኛ ችግር እያስከተሉ ባሉ ህጎች ላይ ለማሻሽልና የንግዱን እንቅስቃሴ ለማገዝ የሚያስችል የተጨማሪ እሴት ታክስ ረቂቅ አዋጅ አዋጅ ቁጥር 58/2011 ሆኖ ም/ቤቱ በሙሉ ድምጽ በዋናነት ለገቢ፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እና በተባባሪነት ለህግ፣ ፍትሕና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መርቷል፡፡

በመቀጠልም ም/ቤቱ ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበትን፣ ካሳ የሚከፈልበትን እና ተነሺዎች መልሰው የሚቋቋሙበትን ሁኔታ ለመወሰን የሚያስችል የተሻሻለውን ረቂቅ አዋጅ አዋጅ ቁጥር 59/2011 ሆኖ በሙሉ ድምጽ በዋናነት ለከተማ ልማት፣ ኮንስትራክሽን እና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እና በተባባሪነት ለህግ ፍትህና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴው የተመራ ሲሆን አስተያየት የሰጡ አባላትም ከዚህ በፊት የነበረው ህግ የልማት ተነሺዎችን ተጠቃሚ ከማድረግ ይልቅ ተጎጂ ሲያደርግ የቆየና የመልካም አስተዳር ጥያቄዎችንም ሲያስነሳ የነበረ በመሆኑ ተመጣጣኝና መልሶ ለማቋቋም የሚያስችል እንዲሆን ቋሚ ኮሚቴው አዋጁን በትኩረት መፈተሽ እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡

ም/ቤቱም በውሎው አገሪቱ ቀልጣፋ የጉምሩክ አስተዳደርና ውጤታማ ህጎች አተገባበር በመዘርጋት፣ የጉሙሩክ ወንጀሎችን ለመከላከል እና አደገኛ ዕጽ ዝውውርን ለመከላከልና ለመግታት እዲሁም አገራችን በእስራኤል መካከል ያለው ንግድ እንዲጠናከር ብሎም እርስበርስ ለመተባበር የተደረገውን ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበውን አዋጅ ም/ቤቱ አዋጅ ቁጥር 60/2011 አድርጎ በሙሉ ድምጽ በዋናነት ለውጭ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በተባባሪነት ለገቢ፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮጭ ቋሚ ኮሚቴው መርቷል፡፡

በመጨረሻም ም/ቤቱ አገሪቱ በቱሪዝም ዘርፍ ልምድ እንዲለዋወጥ የሚያስችል እና ለመተባበር የተደረገውን ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ አዋጅ ቁጥር 61/2011 ሆኖ በሙሉ ድምጽ በዋናነት ለውጭ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በተባባሪነት ለሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እንዲሁም በግብርናም ዘርፍ ለመተባበር የተደረገውን ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበውን ረቂቅ መርምሮ አዋጅ አዋጅ ቁጥር 62/2011 ሆኖ በሙሉ ድምጽ በዋናነት ለወውጭ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮጭ ቋሚ ኮሚቴ በተባባሪነት ለግብርና፣ አርብቶ አደር እና አካባቢ ጥበቃ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴዎች መርቷል፡፡