null The House, women and children affairs standing committee noted this while conducted visit at the ministry of women and children.

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሴቶችና ህጻናት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሴቶችና ህጻናት ጉዳዮች ሚኒስቴር መ/ቤት የመስክ ምልከታ አድርጓል፡፡

ሚንስቴር መስሪያ ቤቱ ከ6 ወር እስከ 1 አመት ላሉ ጨቅላ ሕፃናት እና  ከ3 አመት በታች ላሉ ህጻናት የማቆያ ስፍራ በማዘጋጀት አገልግሎቱን ለመስጠት ዝግጅቱን በማጠናቀቅ ላይ መሆኑን ቋሚ ኮሚቴው መመልከት ችሏል፡፡

በሚንስቴር መስሪያ ቤቱ የህጻናት ዘርፍ ሚንስትር ዴኤታ ወ/ሮ አለሚቱ ኡሞድ እንደገለጹት ለእናቶችና ለህጻናት ምቹ ሁኔታን በመፍጠር ደህንነታቸው እንዲጠበቅ ብሎም የእናቶችን የስራ ጫና ለመቀነስ የተለያዩ ተባባሪ እና ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር እንዲሁም የባለሙያ ድጋፍና ክትትልን በማከል ማዕከሉን ለህጻናት ምቹና የማድረጉ ስራ በመሰራት ላይ መሆኑን ገልጸዋል፡

በሚንስቴር መስሪያ ቤቱ በኩል ለመንግስታዊም ሆነ መንግስታዊ ላልሆኑ መስሪያ ቤቶች ይህንን ልምድ ለማስቀጠል የተጀመሩ ስራዎች መኖራቸውንና እናቶችና ህጻናት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ግንዛቤ የመፍጠሩ ስራ በቀጣይ በትኩረት እንደሚሰራም አብራርተዋል፡፡

ይሁን እንጂ አገልግሎቱን ለመጠቀም የሚያስችል የትራንስፖርት አገልግሎት ችግር እንዳለ ሚንስትር ዴኤታዋ አንስተው ችግሩን ለመቅረፍ የተሄደ ርቀት ቢኖርም የቋሚ ኮሚቴው ድጋፍና ክትትል ያስፈልጋል ብለዋል፡፡   

ቋሚ ኮሚቴው በበኩሉ ሚንስቴር መስሪያ ቤቱ ረቂቅ ጋይድ ላይን አዘጋጅቶ ወደ ክልሎች በማውረድ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን እና የህጻናትን መብትና ደህንነት ከማስጠበቅና አዋጁን ተግባራዊ ከማድረግ አኳያ ህጻናትን ለመቀበል የሚያስችል በቂ ዝግጅት ማድረጉን በጥንካሬ ተመልክቶታል፡፡

የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ወ/ሮ እምዬ ቢተው ሚንስቴር መስሪያ ቤቱ የህጻናት ማቆያ በማዘጋጀትና ለሌሎች ተቋማት የተሻለ ተሞክሮ ከማጋራት፣ ሌሎችን ተከታትሎ ከመደገፍ  እንዲሁም አገልግሎቱ ለታለመለት አላማ እንዲውልና ህጻናት ወደ ማዕከሉ መጥተው እንዲገለገሉ የማድረጉ ስራ ወደ ተጨባጭ ተግባር እንዲገባ የአመለካከት ለውጥ በማምጣቱ ላይ ሰፊ ስራ መሰራት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡