null The Houses elected new female president.

ምክር ቤቶቹ አምባሳደር ሳህለ ወርቅ ዘውዴን የአገሪቱ ርዕሰ ብሄር አድርገው መርጠዋል፡፡

5ኛው የህዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን በ2ኛው ልዩ የጋራ ስብሰባው አምባሳደር ሳህለ-ወርቅ የአገሪቱ ርዕሰ ብሄር አድርጎ መርጠዋል፡፡  

የቀድሞው የሪፐብሊኩ ፕሬዘዳንት ዶ.ር ሙላቱ ተሸመ የመተካካት መርህን በተመለከተ  ከአምስት ዓመት የስራ ዘመን  አገልግሎት በኋላ  በፍቃደኝነት የስራ  ስንብት በምክር ቤቶቹ ተቀባይነትን አግኝቶ በምትካቸው አምባሳር ሳህለ ወርቅ ዘውዴ  በእጩነት ቀርበው በምክር ቤቶቹ ሙሉ ድምጽ አግኝተው  የአገሪቱ ርዕሰ ብሄር በመሆን ተመርጠዋል፡፡

ክቡር ዶ.ር ሙላቱ ተሸመ  ላለፉት ዓመታት በነበራቸው የኋላፊነት ዘመን አገራቸውን በቅንነትና በታማኝነት የአገሪቱ ርዕሰ ብሄር ሁነው ሲያገለግሉ የቆዩ ሲሆን በተለይ ላለፉት 5 ዓመታት ውስጥ 3ቱ ዓመታት በአመዛኙ አገራችን በትልልቅ ፈተናዎች ስጋት ውስጥ ወድቃ እንደነበረችና  ብሄራዊ ደህንነቶች ላይም ውስብስብ የሆነ አደገኛ የሆነ ስጋት አንጃብቦባት እንደነበረም  አስረድተዋል፡፡

እንደ ዶ.ር ሙላቱ አገላለጽ የዜጎችን የዲሞክራሲ የልማት ፍትሃዊ ተጠቃሚነትነና የህግ የበላይነት ጥያቄ ለመመለስ ባለመቻላችን በህዝብ በተቀሰቀሰው ቁጣ እንደ አገር መቀጠላችን ጥያቄ ውስጥ ያስገባበት እንደነበረም ገልጸዋል፡፡

በተለይ ከ6 ወራት  በፊት አገራችን በመስቀለኛ መንገድ ላይ ተስፋ መቁረጥ የጨለማና የብርሃን ጭላንጭን  ይታይባት እንደነበረና ልጆቿን አድኑኝ እያልች ትጣራ እንደነበረም ሰፋ ያለ ገለጻ ሰጥተዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት በአገራችን የተስፋ ጎህ ቀዶ  የጸደይ ወቅት በመድረሳችን በ10ሺዎች የሚቆጠሩ ታራሚዎች መፈታታቸውና መንግስትን በመቃወም በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚኖሩ ተደራዳሪ የፐለቲካ ፓርቲዎች ወደ አገራቸው ገብተው ያመኑበትን የፖለቲካ አማራራጭ በነጻነት በማቅረብ እንዲሳተፉ የሚያስችሉ ሁኔታዎች እንደ ፈጠረላቸውም በዝርዝር አብራርተዋል፡፡

የአገራችን ሰላምና አንድነት ያው ለማድረግ አብረን በጋራ የጀመርነውን የለውጥ ጉዞ ለማስቀጠል እርስ በእርሳችን በመደማመጥና በመተሳሰብ የሚለያዩንንና ጠብ አጫሪነት በመተው አንድነታችን አጠናክረን በማስቀጠል ታላቅ የሆነች አገር ለመገንባት ክብርት ፕሬዘዳንት አምባሳደር ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ከሰላም ውጭ ምንም አማራጭ የለንም ብለዋል፡፡

ለአገሪቱ ርዕሰ ብሄር በመሆን በሁለቱም ምክር ቤቶች  የተመረጡት ክብርት ሳህለ ወርቅ በተለያዩ አገራት አምባሳደርና ልዩ መልዕክተኛ ሁነው ሲያገለግሉ የቆዩ ሲሆን በዛሬው እለት የአገሪቱ ርዕሰ ብሄር በመሆን ተመርጠው ህዝብን በታማኝነትና በቅንነት ለማገልገል ቃለ ማሕላ ፈጽመዋል፡፡