null The Inquiry Board urge the public to cooperate with law enforcement organs to contain Covid-19.

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈፃፀም መርማሪ ቦርዱ በህገ መንግስቱ የተሰጠውን ሃላፊነትና ተግባር ለመወጣት በሚያደርገው እንቅስቃሴ የህብረተሰቡ እና የህግ አስፈፃሚው አካል እግዛ ሊያደርጉ እንደሚገባ አስገነዘበ፡፡

ቦርዱ የአዋጁን አፈፃፀም ለመከታተልና ለመቆጣጠር  የሚያስችል ዝርዝር እቅድ የድርጊት መርሃ ግብር ላይ ውይይት አድርጓል፡፡

በውይይቱ ወቅት የቦርዱ ሰብባቢ የተከበሩ አቶ ጰጥሮስ ወ/ሰንበት  ወረርሽኙ ለመግታት የተደነገገ አፈፃፀም ደንብ ተግባራዊነት ህብረተሰቡ እገዛ ካላደረገ ችግሩ እየሰፋ ሄዶ የመከላከሉን ሥራ ውስብስብ እንደሚያደርገው ገልፀው፡ ህብረተሰቡ የወጣውን ደንብ የማያከብር ከሆነ በወጣው የአፈፃፀም ደንብ መሠረት ተጠያቂ ሊሆን እንደሚችል አሳስበዋል፡፡

ቦርድ የኮረና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈፃፀም ደንብ የተደነገጉ ክልከላዎች ተግባራዊነታቸውን  ከመከትታተልና ከመቆጣጠር  ባሻገር በቫይረሱ ተጠርጥረውና ቫይረሱ ተገኝቶባቸው በኳራንቲንና በለይቶ ማቆያ ያሉ ዜጐች አያያዝን በአካል በመገኘት ጭምር  እንደሚጐበኝ ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም ቦርዱ ይህንን ወረርሽኝ ለመቆጣጠርና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ የጤና ባለሙያዎች ከፍተኛ ሃላፊነት እየተወጡ ባሉበት ሁኔታ ያለውን የሰብዓዊ መብት አያያዝንም በቅርበት የሚከታተል መሆኑን ተጠቁመዋል፡፡

የቦርዱ ም/ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ ዳባ በበኩላቸው   በህገ መንግስቱ መሠረት የተቀመጠውን አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ   ለማስፈፀም ሥልጣን የተሰጠው አካል ሥራውን በተገቢው እየሠራ መሆኑን ቦርዱ በሚገባ ይቆጣጠራል፣ በመሆኑም አላግባብ መብታቸው የተጣሰና በህግ ቁጥጥር ሥር የዋሉ ግለሰቦችን ሥም ዝርዝር  በተለያዩ የመገናኛ ዜዴዎች ይፋ ያደርጋል ነው ያሉት፡፡

በመጨረሻም ህብረተሰቡ ለወረርሽኙ ከፍተኛ ግምት በመስጠት በመንግስትና በዘርፉ ባለሙያዎች የሚተላለፉትን የጥንቃቄ መልዕክቶች ተግባራዊ በማድረግ የራሱንና የህብረተሰቡን እንዲሁም የሃገርን ደህንነት በመጠበቅ የዜግነት ግዴታውን እንዲወጣ የቦርዱ አባላት ጠይቀዋል፡፡