null The standing committee noted Ethiopian Geological survey Authority to solve its problem in leadership competence.

የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ በአመራር የአቅም ውስንነት ምክንያት ለዝቅተኛ አፈፃጸም መዳረጉን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተፈጥሮ ሃብት ልማትና አካባቢ ጥበቃ  ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገለጸ፡፡

ቋሚ ኮሚቴው የተቋሙን የ2010 ዓ.ም በጀት አመት የዘጠኝ ወራት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ገምግሟል፡፡

ተቋሙ በለውጥ ሰራዊት ግንባታ፣ በመልካም አስተዳደር እንዲሁም በኪራይ ሰብሳቢነት በኩል የሚታዩበትን ውስንነቶች ለመቅረፍ አቅዶ የተንቀሳቀሰ ቢሆንም ያቀደውን ማሳካት እንደልቻለ ቋሚ ኮሚቴው ጠቅሷል፡፡

የጂኦሳይንስ ላቦራቶሪ ማዕከል ISO-17025 እውቅና ለማግኘት መጠናቀቅ የነበረበት በ2007 ዓ.ም ሲሆን ሳጠናቀቅ መቅረቱ፣ በ2010 በዘጠኝ ወር እቅድ እንደሚጠናቀቅ ቢታቀድም አሁንም ስራዎች አልቀው እውቅናውን ለማግኘት እንዳልተቻለ የቋሚ ኮሚቴው አባላት ተናግረዋል፡፡

ከላቦራቶሪ በታቀደው መሰረት እውቅና አለማግኘት ጋር በተያያዘ የኪራይ ሰብሳቢነት አዝማሚያ ሊኖር እንደሚችል አባላቱ ስጋታቸውን አብራርተዋል፡፡

ተቋሙ ለሶስት ተከታታይ አመታት የእቅድ አፈጻጸሙ በዝቅተኛ ደረጃ እንደተፈረጀም የቋሚ ኮሚቴው አባላት  ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ዋና ዳይሬክተር አቶ ማስረሻ ገ/ስላሴ በበኩላቸው ለእቅዱ አፈጻጸም ዝቅተኛ መሆን በሃገራችን ተከስቶ የነበረው የጸጥታ ችግር ባቀድነው መሰረት መስራት እንዳንችል እንዲሁም የሰው ሃይል፣ የተሸከርካሪና የአደረጃጀት ችግር እንቅፋት ሆኖብናል ብለዋል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው በበኩሉ ተቋሙ በጂኦተርማል፣ የብረትና የጅም ስቶን ማዕድናት ጥናት ማካሄድ መቻሉን በጥንካሬ ጠቅሶ፤ የጂኦሳይንስ ላቦራቶሪ በታቀደለት ጊዜ አለመጠናቀቅ፣ የከሰል ድንጋይ ጥናት በሚካሄድባቸው ቦታዎች የአካባቢ ጥበቃ አለማድረግ፣ የኢንዱስትሪ ማዕድናት ፍለጋን በውስንነት ተመልክቷል፡፡

የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ ወ/ሮ ጀምበርነሽ ክንፈ በጂኦሳይንስ ላቦራቶሪ ጉዳይ ላይ ኮሚቴው የችግሩን ስፋትና ጥልቀት ግምት ውስጥ በማስገባት ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት እንደሚያደርግም ገልጸዋል፡፡