null The United States will continue its support to bring about the transformation of the nation that has been started …………. David Price.

የተጀመረውን ሀገራዊ ለውጥ  ከዳር ለማድረስ አሜሪካ ድጋፏን አጠናክራ ትቀጥላለች…………. ዴቪድ ፕራይስ

መስከረም 29 ፣ 2012  ዓመተ ምህረት  ፤ የህዚብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ በዴቪድ ፕራይስ የተመራውን የአሜሪካ ልዑካን ቡድን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

ለልዑካን ቡድኑ በሃገሪቷ የተከናወኑ ቁልፍ የለውጥ ስራዎችን አስመልክቶ ገለጻ ተድርጎለታል፡፡

የልዑካን ቡድኑ በተደረገለት ገለጻ ላይ ተመስርቶ  ሀገሪቷ የጀመረችውን  የለውጥ እንቅስቃሴ ለማስቀጠል አሜሪካ ድጋፏን አጠናክራ እንደምትቀጥል የልዑካን ቡድኑ መሪ ሚስተር ዴቪድ ፕራይስ ገልጸዋል፡፡

የፊታችን ግንቦት 2012 ዓመተ ምህረት   የሚካሄደው ሃገራዊ ምርጫ  ነጻ ፣ ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የበኩላችን አስተዋጽኦ እናደርጋለን ሲሉም የልዑካን ቡድን መሪው ተናግረዋል፡፡

መጭው ሃገራዊ ምርጫ ነጻ ፣ ፍትሃዊና ዴሞክራሴያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ መንግስት ዘርፈ ብዙ የሆኑ ስራዎችን ማከናዎኑን አፈ- ጉበኤው አብራርተዋል፡፡

ለዚህም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በአዲስ መልክ መቋቋሙን እንደማሳያ ጠቅሰዋል፡፡

የተጀመረውን ለውጥ በአግባቡ ለማስተዳደር መንግስት ከፍተኛ የሆነ ህዝባዊ  ተሳትፎን ማዕከል  ያደረገ እንቅስቃሴ  ላይ እንደሚገኝ  ነው የተከበሩ አቶ ታገሰ ለልዑካ ቡድኑ የተናገሩት  ፡፡

 ምክር ቤቱ  የህዝቡን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ጥያቄዎች ለማስተናገድና ለመፍታት በምክር ቤቱ በርካታ የለውጥ ስራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል፡፡

ቁልፍ ህዝባዊ የሆኑ ችግሮችን ለመፍታት ምክር ቤቱ በዚህ አመትም ልዩ ትኩረት ሰጥቶ የክትትልና ቁጥጥር ስራዉን እንደሚያጠናክር አቶ ታገሰ  አክለዋል ፡፡

የክትትልና ቁጥጥር ስራው ግቡን ይመታ ዘንድ ምክር ቤቱ የአባላቱን አቅም መገንባቱንም አፈ- ጉባኤው ተናግረዋል፡፡

ምክር ቤቱ ባለፈው በጀት አመት ለውጡን ከዳር ለማድረስ አጋዥ የሆኑ የህግ ማሻሻያዎችን ማድረጉንም አቶ ታገሰ ጠቅሰዋል፡፡

ሃገራዊ ለውጡን በዘላቂነት ለማስቀጠል የአሜሪካ ኤምባሲ ጉልህ ሚና  እየተጫወተ  ሲሆን ኤምባሲው እያደረገው ላለው ጥረት አፈ- ጉባኤው አመስግነዋል፡፡