null The West Bahirdar Air Force has expressed its commitment to intensifying its capacity in the region and beyond.

የምዕራብ አየር ሃይል ባህርዳር ምድብ አገራችን ከቅርበትም ሆነ ከርቀት ጥቃት ለመፈጸም የሚነሳሱ ሃይሎች ቢኖሩ ጉዳት ሳያደርሱ ቀድሞ ማምከን በሚያስችል ደረጃና አቅም ላይ እንደሚገኝ በምድቡ የመስክ ምልከታውን ያካሄደው ቋሚ ኮሚቴ ገለፀ፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግትኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በኢፌዲሪ መከላከያ የምዕራብ አየር ሃይል ባህር ዳር ምድብን ወደ ስፍራው አቅንቶ ጎብኝቷል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው በአካሄደው የመስክ ምልከታ እና ከምድቡ የአየር ሀይል አመራሮችና ከሰራዊቱ አባላት ጋር ባደረገው ውይይት የምዕራብ አየር ሃይል ባህር ዳር ምድብ አሰራሩን ህገ መንግስታዊ ተልዕኮን በብቃት ለመወጣት ወቅቱ በሚጠይቀው ደረጃ የሰራዊቱን ክህሎት ለማሳደግ እና ለማዘመን የተለያዩ የአቅም ግንባታ ስራዎችን በመስራት ላይ እንደሚገኝ መገንዘብ ተችሏል፡፡

ይህም አገራችን ከቅርበትም ሆነ ከርቀት ጥቃት ለመፈጸም የሚነሳሱ ሃይሎች ቢኖሩ ጉዳት ሳያደርሱ ቀድሞ ማምከን በሚያስችል ደረጃ እና በአስተማማኝ ቁመና ላይ የሚገኝ መሆኑን ቋሚ ኮሚቴው አረጋግጧል፡፡

የምእራብ አየር ሃይል ባህርዳር ምድብ አዛዥ የሆኑት ከሎኔል ቸርነት መንገሻ እንደገለፁት በተቋም ደረጃ ሊፈቱ የሚችሉ ቅሬታዎች ትኩረት ሰጥቶ ለመፍታት ጥረት የሚደረግ መሆኑን ገልፀው፤ ከአቅም በላይ የሆኑ ጉዳዮችን ለመፍታት ቋሚ ኮሚቴውም ለሚመለከተው አካል በማሳወቅ እና በመውያየት ጭምር መልስ እንዲያገኙ ሊያግዘን ይገባል ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

የሰራዊቱ አባላት ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በገንዘብ፣ በእውቀት እንዲሁም በጉልበታቸው ጭምር በመደገፍ የችግሮቻቸው ተካፋይ በመሆን የህዝብ ወገንተኝነታቸውን በተግባር እያሳዩ እንደሚገኙም ታውቋል፤

በተጨማሪም ቋሚ ኮሚቴው በአማራ ክልል የኢሚግሬሽን፣ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ቅርንጫፍ /ቤትን የጎበኘ ሲሆን፤ የገመገማቸውን ጥንካሬዎችና ውስንነቶችን ለይቶ በግብረ መልሱ አመላክቷል፡፡

ፓስፖርት ጠያቂዎች በሚጠበቀው አግባብ አገልግሎቱ እንደማያገኙና ይህም ተገልጋዮች ቅሬታ እያነሱ በመሆናቸው ቅሬታዎች ፈጥነው እንዲፈታ በትኩረት እንዲሰራ ቋሚ ኮሚቴው አንስቷል፡፡

የቅርንጫፍ መስሪያ ቤቱ በቴክኖሎጂ በመደገፍ ከዋናው መስሪያ ቤት ጋር በመረጃ መረብ መተሳሰር እንዳለበትና በቴክኖሎጂ አሰራሩን ማዘመን እንደሚገባው ቋሚ ኮሚቴው አሳስቧል፡፡