ምክር ቤቱ ለሀገር በቀል ኢኮኖሚ ትግበራ ውጤታማነት   የጀመራቸውን  ስራዎች መቀጠል እንደሚገባው  ተጠቆመ

 (ዜና ፓርላማ) ሐምሌ 04፣ 2017 ዓ.ም. ፣ አዲስ አበባ፣  ምክር ቤቱ ለሀገር በቀል ኢኮኖሚ ትግበራ ውጤታማነት   የጀመራቸውን  ስራዎች አጠናክሮ  እንዲቀጥል ተጠቁሟል፡፡

ይህ የተጠቆመው፣ ምክር ቤቱ ባዘጋጀው የምርምር እና ጥናት ኮንፈረንስ በቀረበ ጥናታዊ ጽሁፍ  ላይ ሲሆን፣ ምክር ቤቱ የማክሮ ኢኮኖሚው ትግበራ ውጤታማነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሚናውን መወጣት እንዳለበት  አቶ ዳንኤል በየራ ጠቁመዋል፡፡

ለውጤታማነቱ፣ ምክር ቤቱ  የተቋማትን አቅም ክፍተቶች በመፈተሸ ፣ተጠያቂነትን  በማስፈን እና የጥራት ሪፎርሞች ላይ ያተኮረ ስራ ሊሰራ እንደሚገባ ነው አቶ ዳንኤል ያስገነዘቡት፡፡

በሌላ ዜና ፣ በሕግ አወጣጥ ፣ በሕግ ማመጨት እና የሕዝብ ተሳትፎን በተመለከተ የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ  ክቡር አቶ ተስፋዬ ንዋይ ጥናታዊ ጽሁፍ አቅርበዋል፡፡

በጽሁፋቸው የተለያዩ ሀገራትን ተሞክሮ በማጣቀስ ያቀረቡ ሲሆን፣  ምክር ቤቱ ከክልሎች ጋር በመናበብ   ስራ ሊሰራ እንደሚገባው እና ጠንካራ የቅድመ- ምርመራ ስራዎች ላይ ማተኮር እንዳለበት ምክረ-ሃሳብ አቅርበዋል፡፡