ምክር ቤቱ የመሬት መረጃ አያያዝ ሥርዓትን ለማዘመን የሚያስችል ረቂቅ አዋጅን መርምሮ አጸደቀ

 (ዜና ፓርላማ) ግንቦት 12 2017 .ም፤ አዲስ አበባ፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 30 መደበኛ ስብሰባው፤ የመሬት መረጃ አያያዝ ሥርዓትን ለማዘመን የሚያስችል ረቂቅ አዋጅን መርምሮ በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል፡፡

‹‹የከተማ መሬት ይዞታ እና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባ ረቂቅ አዋጅን›› አስፈላጊነት አስመልክቶ የከተማ፣ መሰረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ የተከበሩ እሸቱ ተመስገን (/ሪፖርት እና የውሳኔ ሃሳብ ለምክር ቤቱ አቅርበዋል፡፡

በሀገር-አቀፍ ደረጃ ወጥነት ባለው መልኩ በመላ የሀገሪቱ ከተሞች የሚገኙትን የመሬት ይዞታዎች መረጃ ማደራጀትና በመተግበር ዘመናዊ የአሰራር ሥርዓት ለመዘርጋት ረቂቅ አዋጁ  አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን  የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ አስረድተዋል፡፡

ፈጣንና ዘመናዊ አገልግሎት በመስጠት፤ ሕገ-ወጥ የመሬት ወረራን፣ ብልሹ አሰራርን እና -ፍትሐዊነትን በማስቀረት  ዜጎች የመሬት የይዞታ ባለቤትነትን  ለማረጋገጥ ረቂቅ አዋጁ ጉልህ ሚና ያለው መሆኑን የተከበሩ እሸቱ ተመስገን (/) አያይዘው ገልጸዋል፡፡

ረቂቅ አዋጁ የከተማ መሬት ይዞታና መሬት ነክ ንብረት ማረጋገጥ፣ ምዝገባና አገልግሎት አሰጣጥ ሥራውን ሀገራዊ በሆነ መልኩ ግልጽ፣ ፈጣን፣ ወጥነትና ጥራት ያለው እንዲሆን ለማስቻል እና  አገልግሎት አሰጣጡን በቴክኖሎጂ በማስደገፍ የዜጎችን የመሬት ባለቤትነት የሚያረጋግጥ ነው ሲሉ የተከበሩ ዶክተር እሸቱ ተመስገን  አበክረው አስረድተዋል፡፡

የምክር ቤት አባላት በበኩላቸው፤ በከተማ አስተዳደሮች እና የክልል ከተሞች ያላቸውን ልዩነት እና አንድነት በግልፅ በረቂቅ አዋጁ ማመላከት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ቁራሽ ወይም አነስተኛ መሬቶችን መረጃ ለመያዝ እና ለማስተዳደር (ካዳስተር) ዘመናዊ የመሬት አስተዳደር ስርዓት ለመዘርጋት የዜጎችን የመሬት ባለቤትነት ወሰንን በማይጋፋ መልኩ መሆን እንዳለበት የምክር ቤት አባላት አስገንዝበዋል፡፡

ምክር ቤቱ የከተማ መሬት ይዞታ እና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባ ረቂቅ አዋጅ፤ አዋጅ ቁጥር 1381/2017 አድረጎ በሁለት ተቃውሞ እና በሶስት ተአቅቦ፤ በአብላጫ ድምጽ አፅድቋል፡፡