ምክር ቤቱ የካፒታል ገበያ ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅን አጸደቀ

(ዜና ፓርላማ) ሰኔ 3 ቀን 2013 .. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6 ዓመት የስራ ዘመኑ ባካሄደው 14 መደበኛ ስብሰባው የካፒታል ገበያ ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡

የረቂቅ አዋጁን አስፈላጊነት የገቢ፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ / ያየሽ ተስፋሁነይ ያስረዱ ሲሆን፣ ለሀገር ኢኮኖሚ ዕድገት እና ብልጽግና ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያለው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ሰብሳቢዋ አክለውም የካፒታል ገበያው ባንኮች ችግር ውስጥ በሚገቡበት ወቅት ለመንግስትና ለግሉ ዘርፍ ብቸኛ የፋይናንስ ምንጭ መሆኑን፣ ስራ ላይ ያልዋለ ገንዘብ ያላቸውን ባለሃብቶች ከሚፈልጉት የኢንቨስትመንት አማራጭ ጋር ለማገናኘት እና የአሥር ዓመት የልማት ዕቅዱን ስኬታማ ለማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ከጠቀሷቸው መካከል ይገኙበታል፡፡

ምክር ቤቱም ረቂቅ አዋጁን አዋጅ ቁጥር 1248/2013 አድርጎ በሙሉ ድምጽ አጽድቆታል፡፡