በሕዝብ ተወካዮች /ቤት የሴቶች ኮከስ   እና የሴቶች ሊግ አባላት ሃገር የማዳን ጥሪውን በመቀበል  ከሃገር መከላከያ ሠራዊቱ ጐን እንደሚሠለፉ አረጋገጡ

ነሐሴ 10/2013 / ዜና ፓርላማ አዲስ አበባ፡- በሕዝብ ተወካዮች /ቤት የሴቶች ኮከስ   እና የሴቶች ሊግ አባላት ሃገር የማዳን ጥሪውን በመቀበል  ከሃገር መከላከያ ሠራዊቱ ጐን እንደሚሠለፉ አረጋገጡ፡፡

/ቤቱ በሽብርተኝነት የፈረጃው የህውሃት ታጣቂ ቡድን በሃገር ላይ የቃጣውን ሃገር የማፍረስ አደጋ ለመመከት የተላለፈውን ሃገራዊ ጥሪ በመቀበል  ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የተለያዩ ስንቅና የንጽሕና መጠበቂያ  ቁሳቁሶችን ወደ ግንባር ለመላክ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን የኮኮሱ ሰብሳቢ / አበባዬ ገዛኸኝ  አስታወቁ፡፡

በዝግጅቱ ቆሎ፣ በሶ ደረቅ እንጀራ፣ ኩኪስ እና ለሴት መከላከያ ሰራዊት አባላት የሚውል 97 ሺህ ብር የሚገመት የንፅህና መጠበቂያን ከመንግስትና ከግል ድርጅቶች በማሰባሰብ ለመከላከያ ሰራዊት ለማስረከብ በዝግጅት ላይ ናቸው፡፡

የሴቶች ኮከስ   እና የሴቶች ሊግ አባላት ከዚህ ቀደም ሀገርን ለማዳን በግንባር ላይ ላለው የመከላከያ ሰራዊት ከወር ደመዎዛቸው በተጨማሪ  እያንዳንዳቸው ከኪሳቸው አምስት መቶ ብር በማዋጣት አጋርነታቸውን አረጋግጠዋል፡፡

አባላቱ ከዚህ በተጨማሪ የደም ልገሳ ያደረጉ ሲሆን ወደፊትም ይህን መሰል ድጋፍቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ነው የተናገሩት፡፡