(ዜና ፓርላማ)፤ መስከረም 22፣ 2015 ዓ.ም፤ የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ የተከበሩ አቶ ታገሠ ጫፎ በአሜሪካ ሴናተር የወታደራዊ አገልግሎት ኮሜቴ ሊቀመንበር በሚስተር ጀምስ ኢንሆፍ የተመራው ሚስተር ጆን ሞዝማን እና ማስተር ማሪዮን ማይክ የተካተቱበትን የልኡካን ቡድን ዛሬ ረፋድ በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

በዚሁ ወቅት የተከበሩ አፈ-ጉባዔ አቶ ታገሠ ጫፎ በሀገራዊ ወቅታዊ ጉዳዮች እና በሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙት ዙሪያ ለልኡካን ቡድኑ በቂ ግንዛቤ አስጨብጠዋል፡፡

የተከበሩ አፈ-ጉባዔ ከሴናተር አባላቶቹ ጋር በተወያዩበት ወቅት፤ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ እና መንግስት የሚከተላቸውን የመፍትሄ አቅታጫዎች ጭምር በዝርዝር አብራርተዋል፡፡

የኢትዮጵያን እና የአሜሪካን የሁለትዮሽ የወዳጅነት ግንኙነት ለማጠናከር እንዲሁም፤ ፓርላሜንታዊ ግንኙነታቸውን የበለጠ ለማጎልበት በትብብር የሚሰራ መሆኑን አፈ-ጉባዔ ታገሠ አስረድተዋል፡፡

ሚስተር ጀምስ በበኩላቸው ከተከበሩ አፈ-ጉባዔ በተሰጠው ማብራሪያ ስለ ኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ በቂ ግንዛቤ ማግኘታቸውን ገልፀው፤ በቀጣይ የሁለቱ ሀገራት የፓርላሜንታዊ ግንኙነት ላይ በትብብር ለመስራት ፍላጐት እንዳላቸው አረጋግጠዋል፡፡

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት

በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament

በዩቲዩብ https://www.youtube.com/watch?v=cp_8F5TEeFE

በቴሌግራም https://t.me/ParlamaNews

በትዊተር http://twitter.com/fdrehopr

በዌብሳይት www.hopr.gov.et ይከታተሉ