ዘመናዊ የዳኝነት አገልግሎት መስጠት የህዝቡን መሰረታዊ ችግር ለመቅረፍ ያግዛል -- አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ
ዘመናዊ የዳኝነት አገልግሎት መስጠት የህዝቡን መሰረታዊ ችግር ለመቅረፍ ያግዛል --
አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ
(ዜና ፓርላማ) ሚያዝያ 24 ፣ 2017 ዓ.ም ፤ በኢትዮጵያ ዘመናዊ የዳኝነት አገልግሎት መስጠት የህዝቡን መሰረታዊ ችግር ለመቅረፍ እንደሚያግዝ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ አመላክተዋል::
በዛሬው ዕለት በአፈ ጉባኤው የተመራ ቡድን በኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና በምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉብኝት አድርጓል::
የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሀገራዊ ሪፎርሙን መነሻ በማድርግ እየተገበረ ያለው ዘመናዊ አሰራር ለሌሎች ክልሎችም ተምሳሌት እንደሚሆን የተከበሩ አቶ ታገሰ ጠቀመዋል።
በዚህ መልኩ ዘመናዊ የዳኝነት አገልግሎት መስጠት በየአካባቢው የሚነሳውን የህዝቡን መሰረታዊ ችግር ለመቅረፍ እንደሚያግዝም አስረድተዋል።
የፍትህ ተቋማት በጊዜና በርቀት ያልተገደበ አገልግሎት በመስጠት ለህዝቡ በቀላሉ ተደራሽ ማድረግ እንደሚገባም የተከበሩ አቶ ታገሰ አሳስበዋል።
ከየትኛውም ቦታ ሆኖ የፍርድ ቤት አገልግሎት ማግኘት የሚያስችልና ግልጸኝነት የሰፈነበት ዘመናዊ የዳኝነት አገልግሎት መስጠት የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎች በኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዘዳንት አቶ ገዛሊ አባ ስመል መሪነት ተጎብኝቷል።
በጉብኝቱ ላይ ምክትል አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ሎሚ በዶን ጨምሮ የምክር ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች፣ የፌደራል እና የክልል የፍትህ ተቋማት የስራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል።
(በአበባው ዮሴፍ)
Copyright 2020 - All rights reserved. House of Peoples' Representatives