(ዜና ፓርላማ)፤ ጥቅምት 19፣ 2015 ዓ.ም፤ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሠላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሞሮኮ አፈ-ጉባኤን በቦሌ አየር ማረፊያ ተገኝተው ተቀብለዋል።

የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ የተከበሩ ዶ/ር ፈቲህ ማህዲ እና የውጭ ግንኙነት ንዑስ ኮሚቴ ተወካይ የተከበሩ አምባሳደር ዶ/ር ቶፊቅ አብዱላሂ ዛሬ ጠዋት በቦሌ አየር ማረፊያ ተገኝተው የሞሮኮ አፈ-ጉባኤ ሚስተር ራቺድ ታልቢ ኤል አል አላሚን ተቀብለዋል፡፡

የሞሮኮ አፈ-ጉባኤ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት ለቀድሞው የሞሮኮ ንጉስ ሀሰን II (ሁለተኛ) የሚበረከተውን የፓን አፍሪካ አዋርድ (Pan African Award) ሽልማት ለመቀበል በወቅቱ የሞሮኮ ንጉስ ሞሀመድ IV (አራተኛ) ተወክለው መሆኑ ታውቋል፡፡

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት

በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament

በዩቲዩብ https://www.youtube.com/watch?v=cp_8F5TEeFE

በቴሌግራም https://t.me/ParlamaNews

በትዊተር http://twitter.com/fdrehopr

በዌብሳይት www.hopr.gov.et ይከታተሉ