የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጽህፈት ቤት የተቋቋመበት ዓላማ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሕገመንግስታዊ ተልዕኮውን ለማሳካት የሚያስፈልጉ ሙያዊ ድጋፍና አስተዳደራዊ አገልግሎቶችን ለመስጠት ነው

ጽህፈት ቤቱ የሚከተሉት ስልጣን እና ተግባራት ይኖሩታል፦

፩/  ለምክር ቤቱ ህግ አወጣጥ፣ ክትትልና ቁጥጥር እንዲሁም ለውክልና ስራ የሚያስፈልጉ ሙያዊ ድጋፍና አስተዳደራዊ አገልግሎቶችን ይሰጣል፤

፪/ ለምክር ቤቱና ምክር ቤቱ ለሚያቋቁማቸው ኮሚቴዎችና ሌሎች ውስጣዊ አካላት አጠቃላይ  ሙያዊና አስተዳደራዊ አገልግሎት ይሰጣል፤

፫/  የፌደራል ነጋሪት ጋዜጣን ያስተዳድራል፤

፬/  የምክር ቤቱን የህዝብ ግንኙነት ተግባራት ያከናውናል፤

፭/  ተቋማዊ ቀጣይነትን ያረጋግጣል፤

፮/ ለምክር ቤቱ አባላት እና አካላት በህግ የተወሰኑ ጥቅማጥቅሞችን እና ልዩ መብቶችን ያስፈጽማል፤

፯/ የምክር ቤት አባላት መኖሪያ ቤቶችን ያስተዳድራል፣ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመመካከር ፀጥታና ደህንነት መከበሩን ይከታተላል፤ በማንኛውም የምክር ቤቱ ቅጥር ግቢ ፀጥታና ስነስርዓት መከበሩን ያረጋግጣል፤

፰/   የምክር ቤቱን በጀት ያዘጋጃል፤

፱/ ለምክር ቤቱ አካላትና አባላት የቤተ መጽሃፍት፣ የምርምር፤ የመረጃ እና ዶክሜንቴሽን አገልግሎት ይሰጣል፤

፲/   የአቅም ግንባታ ስራዎችን ይሰራል፤

፲፩/  ለምክር ቤቱና ለምክር ቤቱ የተለያዩ አካላት የቃለጉባኤ፤ የአዳራሽ አገልግሎት፤ የህትመትና ሌሎች የኮንፈረንስ አገልግሎቶች ይሰጣል፤

፲፪/  ለምክር ቤቱ አባላትና አካላት የትራንስፖርት አገልግሎት ይሰጣል፤

፲፫/  የንብረት ባለቤት ይሆናል፣ ውል ይዋዋላል፣ በስሙ ይከሳል፣ ይከሰሳል፤

፲፬/ ዓላማውን ለማሳካት የሚረዱ ሌሎች ተዛማጅ ተግባራትን ያከናውናል።