ኡሳሜ ሞሀመድ

የተከበሩ አቶ ኦሳሜ መሐመድ ሙሁመድ

Biography

የተከበሩ አቶ ኡሳሜ መሐመድ በወጣቶች ልማትና እድገት ፣ በስራ ፈጣሪነት ፣ በኢኮኖሚ እና የፖሊሲ ልማት የአስር አመታት ሰፊ ልምድ ያለው ወጣት የአካባቢ እና የማህበራዊ ልማት አዋቂ ነው። 

ኡሳሜ በዘላቂ ልማት ጥናቶች ሁለተኛ ድግሪ እና በሃይድሮሊክስ ምህንድስና የመጀመሪያ ድግሪውን አጠናቋል።

ኡሳሜ ባለፉት 10 አመታት በማህበራዊ ልማት እና በአካባቢያዊ እድገት ዘላቂነት ላይ በንቃት እየሰራ ሲሆን በተለይም የገጠር ማህበረሰቦችን የአየር ንብረት ለውጥ በውሃ ጥበቃ ፣ በዘመናዊ ግብርና ፣ በፖሊሲ ቅስቀሳ እና ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ዜጎች የውሃ አቅርቦትን ተደራሽ እና ተጠቃሚ ለማድረግ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል። 

ወጣት ኡሳሜ መሐመድ በወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ ፣ በኢኮኖሚ ፍትህ ፣ በአየር ንብረት ፣ በአርብቶ አደር ልማት እና በኢኮኖሚ እድገት ለበለፀገች ኢትዮጵያ በከፍተኛ ንቃት እና ተነሳሽነት እየተጋ ያለ ብርቱ ዜጋ ነው።

Intervention of the Member

votes.