ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከየወረዳው ለተውጣጡ 713 ሰልጣኞች በግዮን ሆቴል እየተሰጠ የሚገኘው ይህ ስልጠና፤ ተባባሪ አካላቱ በየወረዳቸው የሚገኙ ተሳታፊዎችን በመለየት ሂደት ውስጥ ለኮሚሽኑ እገዛ እንዲያደርጉ አቅማቸውን ለማጎልበት ታስቦ ነው፡፡

በተጨማሪም በስልጠናው መርሃ ግብር መሰረት ዛሬ እየተሰጠ ያለው ስልጠና ተባባሪ አካላቱ በሀገራዊ ምክክር ሂደት ላይ መሰረታዊ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ያለመ ነው፡፡ 

ስልጠናው በሀገራዊ ምክክር ፅንሰ ሀሳብ እና ምንነት እንዲሁም ስለኮሚሽኑ ዓለማ፣ ተግባራትና እና የወደፊት አቅጣጫዎች ትኩረት የሚያደርግ  መሆኑን ከኮሚሽኑ የማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡- 
በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament 
በዩቲዩብ https://www.youtube.com/@FDREHOPR 
በቴሌግራም https://t.me/ParlamaNews 
በትዊተር http://twitter.com/fdrehopr 
በዌብሳይት www.hopr.gov.et ይከታተሉ።