በኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ልማት፣ ሥራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ከኢፌዴሪ የኢኖቬሽንና የቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር ባካሄደው የትውውቅ መድረክ የግሉንና የመንግሥትን አገልግሎቶች በቴክኖሎጂ በማዘመን የሀገሪቱንና የሕዝቡን ከፍታ ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት መሰራት እንደሚገባ አሳስቧል፡፡

የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ ነገሪ ሌንጮ (/) በተዘጋጀው የትውውቅ መድረክ ለቋሚ ኮሚቴው በተሰጡ ዋና ዋና ተግባራት፣ ከአስፈፃሚና ተጠሪ ተቋማት በሚጠበቁ ሥራዎች እንዲሁም በሚኖራቸው የግንኙነት ሥርዓት ዙሪያ ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ማብራሪያ አቅርበዋል፡፡

በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በኩል በቴክኖሎጂ ዘርፍ በሚሰሩ ጥናትና ምርምር፣ የዲጂታል ኢኮኖሚን የማረጋጋጥ፣ የኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ላይ ቅንጅታዊ አሠራርን የማስፈን፣ በተመረጡ ጉዳዮች ላይ የመሰረተ ልማት ግንባታን የማከናወን እንዲሁም የሪጉላቶሪ ተግባራት ዙሪያ ላይ ማብራሪያ ቀርቧል

የኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ሚንስቴር ሚንስትር ክቡር በለጠ ሞላ (/) እንደገለጹት ተቋማቸው በህዝብና በመንግስት የተጣለበትን ሀላፊነት ከቋሚ ኮሚቴው እና ከተጠሪ ተቋማት ጋር ተጋግዞና ተቀናጅቶ በመስራት ሀለፊነቱን እንደሚወጣ አረጋግጠዋል፡፡

በሚፍታ ኪያር