"በኢትዮጵያ ፍትሕ እና ርትዕ እንዲረጋገጥ ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል"
ሀገራዊ የፍርድ ቤቶች የለውጥ ፍኖተ ካርታና የፍትሕ ተቋማት ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አፈፃፀም ላይ ውይይት ተካሄደ
------------------------
(ዜና ፓርላማ) ሚያዝያ 25፣ 2017 ዓ.ም፤ በኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አዘጋጅነት ሀገራዊ የፍርድ ቤቶች ፍኖተ ካርታና የፍትሕ ተቋማት ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አፈፃፀም ላይ ውይይት ተካሄደ።
በውይይት መድረኩ ላይ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ታገሠ ጫፎ እና ምክትል አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ሎሚ በዶን ጨምሮ የምክር ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች፣ የክልል ምክር ቤቶች አመራሮች እንዲሁም የፌዴራል እና የክልል ፍርድ ቤቶችና የፍትሕ ተቋማት አመራሮች ተሳትፈዋል።
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት "የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የለውጥ ፍኖተ ካርታ አፈጻጸምን" በተመለከተ የተዘጋጀ ፅሑፍ ለመድረኩ ተሳታፊዎች ያቀረቡ ሲሆን፤ በቀጣይም ሌሎች የመወያያ ፅሑፎች ቀርበው ውይይት የሚደረግባቸው ይሆናል።
Copyright 2020 - All rights reserved. House of Peoples' Representatives
Sign In