"ጥናትና ምርምር ለአንድ ሀገር የሚኖረው ጠቀሜታ የጎላ ነው" የተከበሩ ታገሰ ጫፎ
"ጥናትና ምርምር ለአንድ ሀገር የሚኖረው ጠቀሜታ የጎላ ነው" የተከበሩ ታገሰ ጫፎ
(ዜና ፓርላማ) ሐምሌ 3 ቀን፣ 2017 ዓ.ም.፤ አዲስ አበባ ፤ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ ጥናትና ምርምር ለአንድ ሀገር ኢኮኖሚያዊ ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ዕድገት ጠቀሜታው የጎላ ነው ብለዋል።
አፈ-ጉባኤው ይህን ያሉት በአምስተኛው ዓመታዊ የፓርላማ ጥናትና ምርምረ ኮንፈረንስ የመክፈቻ ንግግር ባደረጉበት ወቅት ነው።
በንግግራቸውም ምርምር ለማንኛውም ሀገራዊ ልማትና ዕድገት መሠረት ነው ያሉ ሲሆን እንደ ተቋም ብሎም እንደ ሀገር ተፈላጊውልን ለውጥ ለማስመዝገብ ጥናትና ምርምር ፉይዳዉ የጎላ መሆኑን አንስተዋል።
አክለውም ምርምሮች ችግሮች በሚያገኘው ጊዜ ከመፍታት ባለፉ አዳዲስና አማራጮችን መፍትሄምን ለመጠቆም እንዲሁም ዕውቀት ላይ የተመሰረቱ ውሳኔዎችን ለመወስን የሚያስችል ነው ብለዋል።
እንዲሁም የጥናትና ምርምር ባህልን በማዳበር ልህቀትን በተግባር ማዋል ቀጣይነት ላለው ዕድገት ወሳኝ መሆኑን አፅንኦት የሰጡበት ነው።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ህግ አውጪ እንደመሆኑ መጠን የሚያወጣቸው ህጐች፣ የሚወሰናቸው ውሳኔዎች እና አፈፃፀምቹ በጥናትና ምርምር ላይ የተመሰረቱ ሊሆኑ እንደሚገባ በማንሳት በዚህም መሠረት ጥናትና ምርምሮች ለህግ አውጪው አካል ሚናው የጎላ ነው ብለዋል።
በዚህም መሠረት የዘንድሮ የፓርላማ ጥናትና ምርምር ኮንፈረንስ ለ5ኛ ጊዜ "ፓርላማዊ ተግባራትን ማጠናከር ለአካታች አስተዳደር ፣ ለሀገር በቀል ዕውቀትና ለዘላቂ ልማት ! " በሚል መሪ ቃል በአድዋ ሙዚየም መሰብሰቢያ አዳራሽ እየተካሄደ ይገኛል።
Copyright 2020 - All rights reserved. House of Peoples' Representatives