“Happy Ethiopian New Year!”
<<እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሳችሁ>>
የተከበሩ አፈ-ጉባዔ ታገሠ ጫፎ
ዜና ፓርላማ ጰጉሜ 05 ቀን 2012 ዓ/ም ፡- የኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ዋና አፈ ጉባዔ ክቡር አቶ ታገሠ ጫፎ በሃገርና ከሃገር ውጪ ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እንኳን ለአአዲሱ አመት አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞታቸውን ገለፁ፡፡
አፈ-ጉባዔ በዛሬው እለት በጽ/ቤታቸው በሰጡት በዚሁ የመልካም ምኞት መግለጫቸው አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የብልፅግና እና የትብብር እንዲሁም የአንድነት እንዲሆን ያላቸውን ልባዊ ምኞት ገልፀዋል፡፡
ባሳለፍነው 2012 ዓ/ም አብነታዊና እና ጥሩ ነገሮች መሠራታቸውን ያስታወሱት ክቡር አፈ-ጉባዔ፣ የህዳሴ ግድብን የተሳካ የመጀመሪያ ዙር የውሃ ሙሌት በምሳሌነት ጠቅሰዋል፡፡ እንደዚሁም በሃገር ደረጃ ከተከናወኑት ኘሮጀክቶች ጐን ለጐን አዲስ አበባ የተከናወነውን የሸገር ኘሮጀክት አፈፃፀም በዋና ለአብነት አስረድተዋል፡፡
ክቡር አፈ ጉባዔ አክለውም እንዳሉት ባሳለፍነው 2012 ዓ/ም ከሃገራችን ህዝቦች ባህል፣ ዕሴት እና ወጐች ወጣ ያሉ ነገሮችም ተከስተዋል፡፡ ይሁን እንጂ ችግሮችን በአብሮነት መንፈስ በመፍታት የሚታወቀው የሀገራችን ሕዝብ አላስፈላጊ ድርጊቶችን የሚያርምበት ዓመት እንዲሆንም ጠይቀዋል፡፡
ሁላችንም ቀና ሆነን ከተሳሰብን፣ ቅን ልቦች ከበዙ፣ ለበጐ ነገር ከተነሳን፣ በጋራ ከቆምን፣ ሐሳብ ለሐሳብ ተግባብተን የጀመርነውን የከፍታ ጉዞ ወደ ዳር ማድረስ እንችላለን ያሉት አፈ-ጉባዔው መጪው ዓመት ለኢትዮጵያዊያን የስኬት፣ የደስታ እና የብልጽግና እንዲሆን በድጋሚ ተመኝተዋል፡፡
Copyright 2020 - All rights reserved. House of Peoples' Representatives