የሴቶች ኮከስ

1/ የሴቶች እና ህፃናት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተግባርና ኃላፊነት እንደተጠበቀ ሆኖ የሴቶች ኮከስ የሚከተሉት ተግባራት

ይኖሩታል፦

) የሴት የምክር ቤት አባላት የልምድ ልውውጥ ያካሄዳል፤

) የሴቶች መብትና ተጠቃሚነትን በሚመለከቱ የተለያዩ አጀንዳዎች ምክክር ያካሄዳል፤

) የአቅም ግንባታና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን ያከናውናል፤

) ከክልል ሴቶች ኮከሶች ጋር ግንኙነት ያደርጋል።

2/ የሴቶች ኮከስ ተጠሪነት ለአፈጉባዔው ይሆናል፣ የኮከሱ ዝርዝር አደረጃጀትና አሰራር በዚህ ደንብ መሰረት በሚወጣ

መመሪያ ይወሰናል።

  • Responsive Image
  • Responsive Image

null Caucus members: call for more close cooperation with caucus in regional councils.

የፓርላማ ሴቶች ተመራጭ ኮከስ የሴቶችን ተሳታፊነትና ተጠቃሚነትን በሁለንተናዊ መልኩ ለማረጋገጥ ከክልሎች ጋር የሚሰራቸውን ስራዎች ማጠናከር እንዳለበት የኮከሱ አባላት ገለጹ፡፡

ኮከሱ በቢሾፍቱ ከተማ የ2010 በጀት ዓመት የ6 ወራት የዕቅድ አፈጻፀም ሪፖርትን ገምግሟል፤ ነባሩን የኮከስ አመራርም በአዳዲስ አስፈጻሚዎች ተክቷል፡፡

ሪፖርቱን ያቀረቡት የኮከሱ ም/ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ አልማዝ መሰለ በበጀት አመቱ የኮከሱ የስራ እንቅስቃሴን በህዝብ ዘንድ እንዲታወቅ የማድረግ፣ በባህር ዳር፣ በጂማ፣ በሀዋሳ፣ በመቀሌና በአሶሳ ዩኒቨርሲቲዎች በሴት ተማሪዎች የትምህርት ተሳትፎ  ላይ የዳሰሳ ጥናት መካሄዱን ገልጸዋል፡፡

በሀገሪቱ በአንዳንድ ቦታዎች በተከሰቱ ችግሮች ላይ ሴቶች ከማንኛውም የህብረተሰብ ክፍል ይበልጥ ተጎጂ በመሆናቸው ሴቶችና ሰላም በሚል ርዕስ ስልጠና መሰጠቱን፣ በኦሮሚያና በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል በተከሰተው ግጭት የተፈናቀሉ የህብረተሰብ ክፍሎችን ኮከሱ በአካል ተገኝቶ መጎብኘቱንና በአይነት 350,000 ሺህ ብር የሚያወጣ ድጋፍ ማድረጉንም አብራርተዋል፡፡

በሌላ በኩል ለኮከሱ መጠናከር የአባላት ተሳትፎ አናሳ መሆን፣ ዕቅዱ ላይ በተቀመጠው መሰረት መደበኛ ስብሰባዎችን አለማድረግና በሚደረጉ ስብሰባዎች ላይም የአባላት ተሟልቶ አለመገኘት ይህም በሚሰጡ አንዳንድ ስልጠናዎች ላይ መስተዋሉን በአፈጻፀም ውስንነት አንስተዋል፡፡

በቀጣይም የኮከሱን አመራርና አባላትን የማጠናከር፣ በአገሪቱ በሚወጡ አዋጆች እና አስፈጻሚ መ/ቤቶች በሚያቀርቧቸው ሪፖርቶች ላይ የሴቶችን ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ስለመሆናቸው ተገቢው ክትትል የማድረግና ግብረ መልስ የመስጠት፣ ቅንጅታዊ አሰራርን የማጠናከር፣ የኮከስ አባላትን በአቅም ግንባታ የማጎልበት፣ የክልል ኮከሶችን የመደገፍ እንዲሁም በህዝብ ግንኙነት የኮከሱን ስራ ተደራሽ የማድረግ ተግባራት በትኩረት አቅጣጫ መቀመጣቸውንም አመልክተዋል፡፡

ተሳታፊዎች በበኩላቸው የፓርላማ ኮከስ የተሻለ ተግባራትን ያከናወነ ቢሆንም መሄድ የሚገባውን ያህል ርቀት እንዳልሄደና በክልሎች ለሚገኙ ኮከሶች ያደረገው ድጋፍም በቂ እንዳልሆነ ጠቁመው፤ ኮከሱ አሁን ካለበት የተሻለ ቁመና ላይ ለመድረስ ይበልጥ መጠናከር እንዳለበት በአስተያየቶቻቸው ገልጸዋል፡፡

ለሪፖርቱ ማጠቃለያ የሰጡት የም/ቤቱ ም/አፈ-ጉባኤና የኮከሱ ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ ሽታዬ ምናለ የኮከሱ አባላት የደሀዋን ሴት ውክልና የያዙ በመሆናቸው ለደሀዋ የአገሪቱ ሴት መብት እና ጥቅም መከበር ከጎኗ መቆምና መታገል እንደሚገባቸው አሳስበዋል፡፡

በመጨረሻም ኮከሱ አጋርን ጨምሮ ከሁሉም መሰረታዊ ድርጅቶችና የሴቶች አደረጃጀቶች የተውጣጡ አዳዲስ የስራ አስፈጻሚና የኮሚቴ አመራሮችን የመረጠ ሲሆን፤ የተከበሩ ወ/ሮ አበባዬ ገዛþኝን የኮከሱ ሰብሳቢ፣ የተከበሩ ወ/ሮ ናፈቁሽ ደሴን ም/ሰብሳቢ በማድረግ እንዲሁም የኮሚቴ አመራሮች በመምረጥ ስብሰባውን አጠናቋል፡፡