የሴቶች ኮከስ

1/ የሴቶች እና ህፃናት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተግባርና ኃላፊነት እንደተጠበቀ ሆኖ የሴቶች ኮከስ የሚከተሉት ተግባራት

ይኖሩታል፦

) የሴት የምክር ቤት አባላት የልምድ ልውውጥ ያካሄዳል፤

) የሴቶች መብትና ተጠቃሚነትን በሚመለከቱ የተለያዩ አጀንዳዎች ምክክር ያካሄዳል፤

) የአቅም ግንባታና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን ያከናውናል፤

) ከክልል ሴቶች ኮከሶች ጋር ግንኙነት ያደርጋል።

2/ የሴቶች ኮከስ ተጠሪነት ለአፈጉባዔው ይሆናል፣ የኮከሱ ዝርዝር አደረጃጀትና አሰራር በዚህ ደንብ መሰረት በሚወጣ

መመሪያ ይወሰናል።

  • Responsive Image
  • Responsive Image

null The parliament should focus on increasing women's participation in upcoming election.

በቀጣይ ምርጫ በፓርላማ የሴቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ ከወዲሁ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ ተጠቆመ፡፡

ሀምሌ 04 ቀን 2011 ዓ.ም. ይህ የተገለፀው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የተመራጭ ሴቶች ኮከስ የ2011 በጀት አመት የእቅድ አፈጻፀም ሪፖርት በቀረበበት ወቅት ነው፡፡

በውይይቱም የኮከሱ አባላትና ተባባሪ ወንድ አባላት የተገኙ ሲሆን፤ የኮከሱን የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ያቀረቡት የኮከሱ ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ አበባዬ ገዛኸኝ በበጀት አመቱ ለፌደራልና ክልሎች ሴት ኮከስ አባላት የአቅም ግንባታ ስልጠና መሰጠቱ፣ የቤተሰብ ህግ ላላወጡ አፋርና ሶማሌ ክልሎች ሕጉን እንዲያወጡ ኮከሱ ድጋፍ ማድረጉን በጠንካራ አፈፃፀም አንስተዋል፡፡

በተመሳሳይም በም/ቤቱ የሚቀርቡ አዋጆችና ሪፖርቶች የሴቶችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ስለመሆናቸው ተገቢው ክትትል መደረጉ፣ በአገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች ተከስተው በነበሩ ግጭቶች ሳቢያ የተፈናቀሉ ዜጎችን በሚመለከት በኤፍ ኤም የሬዲዮ ጣቢያዎች ቀጥታ ውይይት በማድረግ ከአድማጭ ለሚነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያ መሰጠቱ፣ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለመከላከል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች መሰራታቸውንም በጥንካሬ አንስተዋል፡፡

በሌላ በኩል በበጀት አመቱ ኮከሱ በርካታ ተግባራትን ያከናወነ ቢሆንም ስራዎቹን ለህዝብ ተደራሽ ከማድረግ አንፃር ውስንነት መኖሩ፣ ኮከሱ በሚያዘጋጃቸው የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎች ላይ አንዳንድ ክልሎች አለመሳተፋቸው፣ በሁለቱ ክልሎች የቤተሰብ ህግ እንዲወጣ ኮከሱ ድጋፉን ቢያደርግም በክልሎቹ በኩል የቁርጠኝነት ማነስ መኖሩን በእጥረት ከተነሱት ውስጥ ይጠቀሳሉ፡፡

የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ኮከሱ በአገሪቱ አንዳንድ ክፍሎች በተከሰቱ መፈናቀሎች ላይ የኮከሱ አባላት በአካል ጭምር በመገኘትና መረጃውን ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት እንዲደርስ በማድረጉ ረገድ ፈር ቀዳጅ ተግባርን መፈፀሙን በጥንካሬ አንስተዋል፡፡ 

ኮከሱ ያከናወናቸውን ስራዎች በተመለከተ በሚዲያ ማቅረቡ ጥሩ ጅምር ቢሆንም ከዚህ በተሻለና በስፋት ሊሰራበት እንደሚገባ፣ በቀጣይ በአገሪቱ በሚደረገው ምርጫ ላከላይ እስከ ታች ባሉ ም/ቤቶች የሴቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ ከወዲሁ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

ኮከሱ በርካታ ጥሩ ስራዎችን ቢያከናውንም በሴቶች ላይ አሁንም ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችና ጭቆናዎች እየደረሱባቸው ስለሚገኝ ችግሩን ለመቅረፍ አሁንም ኮከሱ ከሚመለከታቸው ከፍተኛ ባለስልጣናት እና አካላት ጋር በመቀናጀት እንዲሁም ቻች ድረስ በመውረድ መስራት እንዳለበትም ነው የተጠቆመው፡፡

የኮከሱ ሰብሳቢና ስራ አስፈፃሚዎች በበኩላቸው ከአባላት የቀረቡ አስተያየቶች ኮከሱ በቀጣይ ለሚያከናውናቸው ተግባራት በግብአትነት እንደሚስዷቸው ገልፀዋል፡፡