የሴቶች ኮከስ

1/ የሴቶች እና ህፃናት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተግባርና ኃላፊነት እንደተጠበቀ ሆኖ የሴቶች ኮከስ የሚከተሉት ተግባራት

ይኖሩታል፦

) የሴት የምክር ቤት አባላት የልምድ ልውውጥ ያካሄዳል፤

) የሴቶች መብትና ተጠቃሚነትን በሚመለከቱ የተለያዩ አጀንዳዎች ምክክር ያካሄዳል፤

) የአቅም ግንባታና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን ያከናውናል፤

) ከክልል ሴቶች ኮከሶች ጋር ግንኙነት ያደርጋል።

2/ የሴቶች ኮከስ ተጠሪነት ለአፈጉባዔው ይሆናል፣ የኮከሱ ዝርዝር አደረጃጀትና አሰራር በዚህ ደንብ መሰረት በሚወጣ

መመሪያ ይወሰናል።

  • Responsive Image
  • Responsive Image

null The Trainings on management and legislation help the House member on their legislation and oversight activities.

በአመራርነት እና በህግ የበላይነት ዙሪያ የተሰጠው ስልጠና የም/ቤት አባላት ለሚያከናውኑት የህግ አወጣጥ፣ ክትትልና ቁጥጥር ተግባራት አጋዥ እንደሆነ ተገለ፡፡ 

ስልጠናው ከጀስቲስ ፎር ኦል ፕሪዝን ፌሎሺፕ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር  ጥር 25 እና 26 ቀን 2011 ዓ.ም በካፒታል ሆቴል የተሰጠ ሲሆን ስልጠናውም በአመራርነት እና በህግ የበላይነት አተገባበር ዙሪያ ትኩረት ያደረገ ነው፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፐብሊክ አድሚኒስትሬሽን እና ዲቨሎፕመንት ማናጅመንት መምህር የሆኑት ረዳት ፕ/ር ቴዎድሮስ ተሾመ በስልታዊ አመራርነት ዙሪያ ሰፋ ያለ ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ስልታዊ መሪዎች መላ ፋላጊዎች እና አርቆ አሳቢዎች እንዲሁም አቅዶ በመፈጸምና እና በውሳኔ ሰጭት የተካኑ መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡

ስልታዊ አመራርነትን በተመለከተ በስድስት አበይት ነጥቦች ላይ ትኩረት አድርገው ለአባላቱ ገለጻ ያደረጉት ረዳት ፕሮፌሰሩ የሩቁን ማየት፣ ሁሉን አለመቀበል፣ መተርጎም፣ መወሰን፣ ማሰለፍ እና መማር እንደሆኑ በዝርዝር አቅርበዋል፡፡ ከምክር ቤቱ ስልጣንና ተግባር ጋር እያገናኙም በእያንዳንዱ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ሰፋ ያለ ትንታኔም ሰጥተዋል፡፡

ስልታዊ መሪ የተለያዩ ሀሳብ የያዙ ባለድርሻ አካላትን ወደ አንድ ሀሳብ እንዲመጡና የጋራ አመለካከት እንዲኖራቸው ትኩረት እንደሚሰጥ የገለጹት ፕሮፌሰሩ መሪው ለስኬት የሚበቃውም ከራሱ አልፎ ሌሎችን ማሳተፍና ማወያየት ሲችል ነው ብለዋል፡፡

በተመሳሳይም ስልታዊ መሪዎች የራሳቸውንም ሆነ የቡድኑን ሽንፈትና ውድቀት ግልጽና ገንቢ በሆነ መንገድ በማጥናት የተሰወረውን ቁልፍ ጉዳይ ለማወቅ ሁለንተናዊ ጥረት እንደሚያደርጉ ነው ያስረዱት፡፡

በጀስቲስ ፎር ኦል ፕሪዝን ፌሎሺፕ ኢትዮጵያ የሲኔር ፖሊሲ አድቮኬሲና አድቫይዘር  ዶክተር ውብሸት ሽፈራው በበኩላቸው በህግ የበላይነት እና አተገባበር ዙሪያ ገለጻ ባደረጉበት ወቅት በየጊዜው የሚወጡ ህጎች በበዙና ባልታወቁ ቁጥር ያልተረጋጋ ማህበረሰብ እንደሚፈጠር ገልጸው በሌላ በኩል ህጎችን በቀላሉ አንብቦ ለመረዳት  በግልጽ ቋንቋ እና  በአጫጭር አረፍተ ነገሮች መጻፍ እንዳለባቸው አስረድተዋል፡፡ ህጎች ሲወጡም ቃለ-ጉባኤና ድርሰት የመሰሉ ጽሁፎች ሊሆኑ አንደማይገባ ጠቁመዋል፡፡

የምክር ቤቱ የኮከስ አባላት በበኩላቸው ከተሰጠው ስልጠና አንጻር በአገሪቱ በሚወጡ አንዳንድ ህጎች፣ መመሪያዎችና ደንቦች ላይ የተወሰኑ ብዥታዎችና ክፍተቶች እንዳሉባቸው ተገንዝበዋል ፡፡

ክፍተት የሚታይባቸው ህጎች ተለይተው ማስተካከያና ማሻሻያ ሊደረግባቸው እንደሚገባ እና በህግ አወጣጥ ዙሪያም የበለጠ ትኩረት መሰጠት እንዳለበት ነው ከስልጠናው የተረዱት፡፡

በሌላ በኩልም ስልጠናው የአመራርነት ጥበብንና የህግ ስርዓት አተገባበርን በተመለከተ በርካታ ቁም ነገሮችን እንደጨበጡ ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም ስራቸውን በእውቀትና በክህሎት እንዲሰሩ፣ ከስልጠናው ያገኙት ትምህርት አቅም አንደሚፈጥርላቸውና  የክትትልና ቁጥጥር ስራቸውን በአግባቡ ለማከናወን የሚያግዝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም ስልጠናው ለሁሉም የምክር ቤት አባላት ቢሰጥ ትልቅ አቅም የሚፈጥር እና ግንዛቤያቸውን የሚያሰፋ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡